ልበ አምላክ ዳዊት በገናውን አነሳና አስሩን ቅኝት ቃኘውና ስለእመቤታችን እንዲህ ብሎ ዘመረ;
እምነ ፅዮን ይብል ሰብ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል ፤ በውስጧም ሰው ተወለደ። መዝ 86:5
v መናፍቃኑ ፅዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ኢየሩሳሌም ብቻ ናት ይላሉ፤ ከመሬት ውስጥ ሰው ይወለዳል እንዴ? አይወለድም ወደፊትም አይወለድም; ዳዊት በውስጧም ሰው ተወለደ ያለው አማናዊ ጽዮን የሆነችውን እመቤታችንን ነው። ዳዊት ለመናፍቃኑ ደገመና እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፤ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት /ዛቲ ይዕቲ ምዕራፍየ ለአለም/ መርጫታለሁና በእርሷም አድራለሁ መዝ 131:13።
ፅዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት ነው፤ እመቤታችን ሀገረ ምስካይ /የመማጸኛ ከተማ/ ናትና። አንድም እመቤታችን ጽዮነ ሥጋ ዘነፍስ; ጽዮነ ሃጥአን ዘጻድቃን ናትና ፤ ጻድቃን እነ አባ ሕርያቆስ እነ አባ ኤፍሬም ተዓምሯን የጻፈው ቅ/ደቅስዮስ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዋጋችንን ታሰጠናለች ብለው። ሃጥዓን እነ ታውፋንያ፤ እነ በላዔ ሰብ ታስምረናለች ብለው ተጠግተውባታልና እመቤታችን ጽዮን በመባል ትጠራለች። አንድም ልበአምላክ ዳዊት ፅዮንን ክበቧት እንዳለ መዝ. [47:12] ሐዋርያቱ እመቤታችንን መሃላቸው አድርገው ከበዋት ለጸሎት ሲተጉ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ ይለናል [የሐዋ. 1.14] አንድም ነብዩ ኢሳያስ ስለ ጽዮን /ስለ ድንግል ማርያም/ ዝም አልልም እንዳለ ኢሳያስ[62:1]
እኛም ተዓምርሽንም በዓይኔ አይቻለሁ ፅዮን ሆይ ስልሽ
ድንግል ሆይ እጠግባለሁ እያልን እንዘምራለን።
ድንግል ሆይ እጠግባለሁ እያልን እንዘምራለን።
ወ ሥ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
የእመቤታችን ፀጋ የፀጋ ልብስ ይሁንልን ፤አሜን [ተክለ መድህን]
7 comments:
GOD BLESS YOU!
Thanks!u tell the better God give u good health n long life time.
God blessyou!!Saturday at 4:18pm via mobile · UnlikeLike ·
Kale hiowt yasemalen may God bless u.Saturday at 5:59pm via mobile · UnlikeLike · 1You like this.
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ! በጣም እናመሰግናለን !!!!!!!!!!!!!
የሕይወትን ቃል ለሁላችንም ያሰማን ፤ አሜን!
Post a Comment