Monday, 28 November 2011

Righteous From paradise



Righteous From paradise


የቅዱሳን ምልጃ ከገነት”

አንድ ወንድሜ ጻድቃንን ከሞቱ ባሗላ  ለምኑልን፤ ጸልዩልን የምትሉት እኛ የምንሰራውን ስራ በምን ያውቃሉ? እንዴትስ ይሰሟችሗል ብሎ ጠየቀኝ።  ወንድሜ የጠየቀኝን ጥያቄ እኔ ሳልሆን መፅሐፍ ቅዱስ መልሶለት ለህሊናው ጥያቄ መልስ አግኝቶበታል፤ ለመሆኑ ጻድቃን ከሞቱ በሗላ እኛ የምንለምናቸውን ልመና እንዴት ይሰማሉ???

 
v   አብርሐም፦ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈ አንድ ታሪክ አለ ሃጥኡ ነዌ በሲኦል እያለ ከሩቅ በገነት አብርሐምን አየውና አብርሐም አባት ሆይ እኔ በሲኦል እሣት እጅግ እየተሰቃየሁ ነውና እባክህን ምላሴን በቀዝቃዛ ውሃ እንዲያርስልኝ አላዛርን ላክልኝ አለው፤ አብርሐምም በኛና በናንተ መካከል ታላቅ ገደል አለ ብሎ መለሰለት፤ ነዌም እንግዲያው በዓለም የሚኖሩ 5 ወንድሞች አሉኝና እባክህን አላዛርን ላከው አለ፤ አብርሐም የሚገርም ቃል ተናገረ ለነሱ ሙሴና ነብያት አሏቸው አለ ይገርማል አብርሐም ሙሴን የት አየው? መቼ ተገናኘው? አብርሐምና ሙሴ በዓለም አልተገናኙም ነገር ግን አብርሐም በአካለ ነፍስ ሆኖ ሙሴ እንደመጣ; መጽሐፍትን እንደጻፈ; ተዓምራትን እንደሰራ; የኤርትራን ባህር እንደከፈለ ያውቅ ነበር!! አዎ በአካለ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን በዓለም የሚከናወነውን ሁሉ ከእኛ በላይ ያውቃሉ; ስለእኛም ይለምናሉ፤ በሲኦል ያለው ነዌ ስለ ወንድሞቹ ከለመነ በገነት ያሉት ፃድቃንማ እንዴት ስለእኛ አይለምኑ?? አብርሐም በአካለ ነፍስ ሆኖ አላዛርና ነዌ በዓለም ምን እንደሰሩ ያውቅ ነበር፤ አላዛር አንተ ችግርን ሁሉ ታገስክ; ነዌ አንተም ምቾትን ሁሉ ተቀበልክ” ያለው አብርሐም በአካለ ነፍስ ሆኖ ምን እንደሰሩ ስለሚያውቅ ነው። አንዳንድ ሰዎች ፃድቃን በአካለ ነፍስ ሆነው እንዴት ያውቃሉ ይላሉ አይደል? ወንጌሉ ይገለጥና ይነበብ በደንብ ያስረዳናል [ሉቃስ 16:19] ነዌ አብርሐምን አነጋገረ; አብርሐምም መለሰለት፤ አብርሐም መናገር መቻሉ ሕያው መሆኑን ያስረዳናል ጌታችንም እኔ የሕያዋን የአብርሐም የይሥሐቅ የያዕቆብ አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለሁም ያለውም ለዚሁ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አለ አሁን በመስታወት እንደሚያይ በድንግዝግዝ እናያለን ያን ግዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን”[1ኛ ቆሮ13:12]
አዎ ቅዱሳኑ ስለሃገራችን ስለዓለም ስለቤተክርስቲያን ስለራሳችን ለምኑልን ስንል ይሰማሉ፤ ቅዱሳኑ ሁሉን ፊት ለፊት በግልጽ ያያሉና!!
ዐለት የተባለውን የሐዋርያት አለቃን ስለእምነታችን ፅናት እስኪ እንለምነው
ከሞቴ በሗላ ስለ እምነታችሁ ፅናት ስለእናንተ እተጋለሁ [2ኛ ጴጥሮስ 1:15]                   
[ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ]
v
ከሞተ ዘመናት ያለፉት ሙሴ ከኤልያስ ጋር በደብረ ታቦር በተገለጸ ግዜ ኤልያስና ሙሴ ከጌታ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ትንቢት ተናገሩ፤ ሉቃስ 9:30። ሙሴ መናገር መቻሉና ትንቢት መተንበዩ ሕያው መሆኑን ያስረዳናል።

v ደመ ሰማዕታት [Martyrdom]
ሰማዕታት ማለት ሰማ መሰከረ ሰማዕት ምስክር ማለት ነው። ደመ ሰማዕታት በታላቅ ድምጽ እየጮሁ ደማችንን በከንቱ ያፈሰሱትን የማትበቀለው እስከመቼ ድረስ ነው”? አሉ [ራዕ 6:9] በታላቅ ድምጽ መጮህ መቻላቸው ሕያዋን መሆናቸውን ያስረዳናል። ደማችንን በከንቱ ያፈሰሱትን የማትበቀለው እስከመቼ ድረስ ነው? ማለታቸው ደማቸውን በከንቱ ያፈሰሱት እነ ዲዮቅልጥያኖስና ሌሎችም ገና እንዳልተቀጡ ስለሚያውቁ ነው። ጌታም ሌሎች ሰማዕታት ስላሉ እንዲታገሱ ነግሯቸው የንጽህና ምልክት የሆነውን ነጭ ልብስ ሰጣቸው።
ሰማዕታት ደማቸውን በከንቱ ስላፈሰሱት ፍርድን ሲጠይቁ  
ስለ እኛ ደግሞ ይለምናሉ።

vዊት፦
 ልበ አምላክ ዳዊት ከሞተ ከብዙ ዘመን በሗላ ስለ ዳዊት ስል
ኢየሩሳሌምን ከጥፋት እጋርዳታለሁ እንዳለ [2ኛ. ነገ19:34] ቅድስቲቱን ከተማ ሃገራችንን ከጠላት እንዲጠብቅልን በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ያሉ ፃድቃን ሰማዕታትን እንለምን።

በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ያሉ የቅዱሳኑ ምልጃ ከእኛና ከሃገራችን ከኢትዮጲያና - ኤርትራ” አይለይ አሜን!


ነብያትን ይስሙ [ሉቃስ 16:19]


ነዌ ባለጠጋው ሃብቱን አከማችቶ
እለት ከእለት ባለም ተመቻችቶ
ይኖር ነበር አምላክን ረስቶ
ደሃው አላዛርም በደጁ ተኝቶ
አንድ ቀን ጌታዬ ያዝንኛል ብሎ
ቀን ይቆጥር ነበር በቁስል ተወርሶ
ቁራሽ ፍርፋሪን አገኛለሁ ብሎ።

ባለጠጋ በልቡ ሳይራራ
በንቀት አየው ሲወጣ ሲገባ
ቀኑ ደረሰና ደሃ ተጠራ
በአብርሃም እቅፍ መልካም ቦታ አገኘ
ነዌ ባለጠጋ ሃብቱ መች ጠቀመው
ቀኑ ሲደርስ እርሱም ሞት አገኘው
መልካም ስላልነበር በምድር የሰራው
በሲኦል ክፉ ሆኖ አገኘው
በስቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን አየው
አላዛርንም በእቅፉ ቢያየው
የጣቱን ጫፍ በውሃ ውስጥ ነክሮ
ምላሴን ቢያርሰው
አብርሃም አባት ሆይ አላዛርን እባክህን ላከው
ብሎ አላዛርን ሻተ በምድር ለናቀው።
አብርሃም መልሶ
አንተ በምድር ሳለህ መልካምን ተቀበልክ
አላዛርም ደግሞ እንዲሁ ክፉውን
ሁሉን ተቀብሏል አሁን ግን ይፅናናል
በኛና በናንተ ታላቅ ገደል ሆኗል።
ነዌ ይህን ግዜ 5 ወንድም አሉኝ
እነርሱም ደግሞ እንደኔ እንዳይሆኑ
አላዛርን ላከው ሁሉን ይንገርልኝ፤
ሙሴና ነብያት ለነርሱ አሏቸው
እነርሱንም ይስሙ መንገድ ይሁኗቸው
ሰምተው ቢፈፅሙት ህይወት ይሁናቸው
ብሎ መለሰለት እኛ እንድንሰማቸው።
            /ተክለ መድህን/ 
በቅዱሳን ላይ በትዕቢት የሚናገር አንደበት ዲዳ ይሁን!
          [መዝሙረ ዳዊት 30:18]

4 comments:

Yeti Mehari said...

Kale hiwot yasemalen yetsadkan yesemaetat yekdusan amalajinet zewetir ayileyen bereketachew yiderbn amen !!!

Aklilu Tegenu said...

GOD bless you!!! That clears many doubts.

Gezahagn Fantahun said...

እግዚአብሔር አምላክ ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረኩ እንዳለ መዝ 88(89) ፡3 ቅዱሳን ከዕረፍተ ሞታቸው በኋላ እንደቀደመው በአጸደ ስጋ እያሉ ሲያደርጉ እንደነበረው የመጾም ፤የመስገድ ፤ ልዬ ልዬ መከራዎችን መቀበል ባይኖርባቸውም አስቀድመው ባደረጉት ተጋድሎ በተሰጣቸውን የማማለድ ጸጋ አምነው ስማቸውን የሚጠሩ ሰዎች ሲድኑበት እናያለን ለዚህም ቆላ 2፡5 ‹‹በስጋ ምንም እንኳ ብርቅ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ ›› እንዳለ ሐዋሪያው ይህም የሚያስረዳን ቅዱሳን ከእረፍታቸው በኋላ ከእኛ የማይርቁ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ አድርገን ከብሉይ ኪዳን 2 ነገ 13፡20 ‹‹ኤልሳዕ ሞቶ ቀበሩትም ከሞዓብም አደጋ ጣዬች በየዓመቱ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር፡፡ ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዬች አዬ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዬው ድኖ በእግሩ ቆመ ›› ነብዬ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት በመዝ 88፡34 ‹‹ኪዳኔንም አላረክስም ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም ››እንዳለ ሐዋሪያው ይሁዳ ከላይ የተገለጸውን ቃል ሲያጠናክር ይሁ 1፡14-16 ‹‹……ስለ ሰው ልጆችም ፈጽመው ይለምናሉ ይፀልያሉ ›› በማለት ቅዱሳን በዚህ ዓለም ስላሉ ሰዎች እንደሚማልዱ የገለጸው፡፡Tuesday at 1:34pm · LikeUnlike · 3Loading...

ዮናስ ዘካርያስ said...

Tewodros Kebede Mekonnen, Yeti Mehari, Genet Salomon and 14 others like this.