ታላቁ መልአክ "በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" አለ። እነሆ የአምላክ ልጆች መላዕክት እጅግ ብዙ ናቸው። ለምሳሌ የሰው ልጅ 3 ነገድ ቢሆንም በዓለም ላይ ከ 6 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ አለ። መላዕክት ደግሞ 100 ነገድ ናቸው። ይህ በጥቂቱም ቢሆን የአምላክ ልጆች መላዕክት እልፍ አእላፋት መሆናቸውን ያስረዳናል።
/1/ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ማለት ምን ማለት ነው? መቼስ መላዕክት እግር የላቸውም አይቆሙም። አይተኙም፤ ታድያ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለት ምን ማለት ነው?
/2/ ስለ ሕዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል ማለት ምን ማለት ነው? መቼስ መላእክት እግረ ስጋ የላቸውምና ሚካኤል ስለ ሕዝቡ ይቆማል ማለት ምን ማለት ይሆን?
No comments:
Post a Comment