ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ!
ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር እሑድ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ። እኔም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት አሰብኩና ባለሁበት ሀገር የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ወይንም የአሜሪካው ኦባማ (የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና) ከሁለት አንዱ ቢሞቱ ኖሮ ሐዘኑ እንዴት ይሆን ነበር? ብዬ አሰብኩ። በሀገሪቱ መገናኛ ዜናው ይሰራጫል ከዚያም በክብር ይቀበራሉ አራት ነጥብ። ከአራት ነጥብ ቢዘል ሐዘኑ አንድ ቀን በቀጥታ ይተላለፋል እንጂ እንግሊዛዊያን በሙሉ ወጥተው ዕንባ አዋጡ ተብለው አይገደዱም ነበር!!
እነሱ ምንቦጣቸው እቴ። ኦባማማ የፍልፍሉን ኮሜዲ መስማት ጀምረዋል አሉ። የታደሉ እየሳቁ ይሰራሉ። የኔ ሙከራ በፍጹም የፖለቲካ ዘፈን ለመጋበዝ አይደለም። የሙዚቃ ስልቱንም አልችልበት። ለፖለቲካ እስክስታ ሲመቱ ከዐይን ያውጣችሁ የተባሉ አሉና ስራ ለሰሪው ብያለሁ። እትብቴ የተቀበረባት ሀገሬ ኢትዮጵያ ግን ሠርጓ ሠርጌ ሞቷ ሞቴ ነው። መቼስ ለእናት ሀገር “ያገባሽስ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ” አይባልም!
“ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ” አሉ እቴጌ ጣይቱ! ይህች ኢቲቪ የምታሳየን ደጋፊውን ብቻ ስለሆነ ጫወታው ፍዝዝ ብሏል። “ያልታደለች ወፍ ዐይኗ በጥቅምት ይጠፋል” እንዲሉ እኛም አልታደልን ዐይናችንና ኢቲቪ ከተጣሉ ቆይተዋል። ሞቅ ደመቅ ካለው ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ እንግሊዝን ፓርላማ እንመለስ። የእንግሊዙን ፓርላማ ስናይ እርስ በእርሳቸው እንደ ጉድ ይከራከራሉ፣ እንደ ጉድ ደጋፊና ተቃዋሚ ይፋለማሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደ ጉድ ቁጭ ብድግ እያደረጉ በጥያቄ ያፋጥጣሉ፤ አልፎ አልፎ ሳቅ ፈገግ የሚያስብል ቃላትን ወርወር ያደርጋሉ! የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ እና የእንግሊዝን ፓርላማ ያየ ይዝናናል የሚባለውም ለዚሁ ነው። እኛ ቤት ግን ይህ ፍጹም ነውር ነው። ደጋፊ በሀገር ውስጥ ተቃዋሚ በአሜሪካ ሆነው በሁለቱም በኩል ምርጥ ምርጥ የተጋነኑ ዜናዎችን ስንሰማ ዐይናችንም ጆሯችንም ሰልችተዋል።
“ጅብ እንኳን ጓደኛውን ይጠራል” አሉ እቴጌ ጣይቱ። ጅብ በለስ ሲቀናው ድምጹን ከፍ አድርጎ ሌሎችን ጅብ ይጠራል። ይህን የመሰለ እንስሳ ሆዳም ማለታችን እጅጉን ይገርማል። እባካችሁ ተለያይቶ መናከስን ሳይሆን እንደ ጅብ ተጠራርቶ መብላትን ለሀገር መስራትን አስተምሩን። እንግሊዛዊያን ስለ ውድ ሀገራቸው ስለ ታላቅዋ ብሪታንያ አንድ አባባል አላቸው። “አንድ ላይ መስጠም ሳይሆን አንድ ላይ መዋኘት አለብን” ይላሉ። እባካችሁ ለእናት ሀገር ስትሉ አንድ ላይ ዋኙ። እባካችሁ ለእናት ሀገር ስትሉ የሐሳብ ፍልሚያ አሳዩን። የልብ ሳይደርስ እድሜ ይደርስ አሉ እቴጌ ጣይቱ።
የማንችስተርና የአርሴናል ልዩነት ጫወታውን ሞቅ ደመቅ ያደርገዋል። ሁሉም የማንችስተር ደጋፊ ቢሆን የኳስ ውበቱ በጠፋ ነበር። ሁሉም የአርሴናል ተቃዋሚ ቢሆን ኳስ ውበትዋን አጥታ መልከ ጥፉ በሆነች ነበር። የኛ ቤት ጫወታ ግን ፈዘዘ። ኢቲቪ የምታሳየን ደጋፊውን ብቻ ስለሆነ ጫወታው ፍዝዝ ቅዝዝ ብሏል። አፈር ስሆን አሁን ማን ይሙት የእንግሊዝ ቻናሎች ቢሆኑ ያ ሁሉ “ዕንባ አዋጡ” የሚል ፕሮግራም የሚተላለፍ ይመስላችኋል? መልሱን ለኢቲቪ ትቻለሁ።
“ሳያርፉ ዐረፉ”
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ላይኛው ሀገር ሄደዋልና የሞተን መውቀስ ለሕሊናም አይመችም። ነፍስ ይማር ማለት ሰዋዊነት ሰብአዊነት ኢትዮጵያዊነት ነው። አንድም ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው። ነፍስ ይማርና በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ 19 ዓመቴ ጀምሮ እረፍት የሚባል ነገር አላየሁምና በሀገሬ ሆኜ የትርፍ ስራ እየሰራሁ ማረፍ እፈልጋለሁ ብለው ነበር። ይህ ቢሳካ ኖሮ ሀገሬ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ጎዳና ዳዴ ማለትዋ በታወቀ ነበር። ምኞታቸው አልተሳካምና ስልጣን በፈቃዱ የለቀቀ ጀግና ሀገሬ እንዳማራት ጎምጅታ እንዳማራት ትቀራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጊዜ እጥረት የተነሳ ማንበብ እየፈለኩ ያላነበብኩት መጻፍ እየፈለኩ ያልጻፍኩት ነገሮች አሉ፤ ወደ ፊት ምን እንደሚሆን አይታወቅምና ከስር ከስሩ ማየት እፈልጋለሁ ብለው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ሞት ቀጠሮ ይዞ ኖሯል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳያስቡት ድንገት የቤተመንግስቱን በር አንኳኩቶ መጣ። የናፈቁትን ረፍት ሳያዩ ዐረፉ። “ሳያርፉ ዐረፉ”
እቴጌ ጣይቱን መለስ ዜናዊ “ሳያርፉ ዐረፉ” ስላቸው ነፍስ ይማር አሉ። ዜና እንዴት ነበር? አልኳቸው ኢቲቪ እንደማይዋጥላቸው ስለማውቅ። አዬ እንደ ስራቸው አሉ እንደለመዱት። እቴጌ ጣይቱ እገሌ እንዲህ ሆነ ሲባሉ “እንደ ስራው” ማለት ይቀናቸዋል። ምንም ይሁን ምንም ወሬ በሰሙ ቁጥር “እንደ ስራው” ይሉ ነበር። ትልቅ አባባል ነው። የሆነው ይሁንና ኢቲቪ የምንከፍተው ግን ምን እንደሚተላለፍ እርግጠኛ ሆነን ነው! “ዕንባ አዋጡ!” የሚል ዜና ለማየት እንደሆነ እኛ ሳንሆን ቴሌቭዥኑም አሳምሮ ያውቃል!!
“ዕንባ አዋጡ!”
~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~
የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!!
ከራሴ ጋ አጠር ያለች ስብሰባ አደረኩና አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። እናቴ ወንድሜን በቀኝ እኔን በግራ አስቀምጣ “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ጸጉር” ትል ነበር ወላድ ሆዷን እየዳበሰች! እኔ ደግሞ “ጨረቃ ካለች እሩጥ እናት ካለች አጊጥ” ብዬ ተረቱን በተረት እመልስላታለሁ። እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ግን “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር የሚለው ተረት አልደረሰባትም። “ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል” እንዲል ሀገሬ አልታደለችምና ደጋፊና ተቃዋሚ ፣ ነጭና ጥቁር ፣ ረጅምና አጭር በሀገሬ ኢትዮጵያ ስማቸው እንጂ ግብራቸው የጠፋ ይመስላል። እኛ ያለን አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ብትሆንም እሷም “በግድ እንባ አዋጡ” የሚል ዜና በዛባት። አንዱ ሲደግፍ ሌላው ሲቃወም ማየት ናፈቀኝ። ደጋፊና ተቃዋሚ ማየት ናፈቀኝ። “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ጸጉር” የሚለውን ተረት ለመተረት በሀገር ቤት ብዙ እናቶች የናፈቁ ይመስለኛል።
ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር እሑድ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ። እኔም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት አሰብኩና ባለሁበት ሀገር የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ወይንም የአሜሪካው ኦባማ (የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና) ከሁለት አንዱ ቢሞቱ ኖሮ ሐዘኑ እንዴት ይሆን ነበር? ብዬ አሰብኩ። በሀገሪቱ መገናኛ ዜናው ይሰራጫል ከዚያም በክብር ይቀበራሉ አራት ነጥብ። ከአራት ነጥብ ቢዘል ሐዘኑ አንድ ቀን በቀጥታ ይተላለፋል እንጂ እንግሊዛዊያን በሙሉ ወጥተው ዕንባ አዋጡ ተብለው አይገደዱም ነበር!!
እነሱ ምንቦጣቸው እቴ። ኦባማማ የፍልፍሉን ኮሜዲ መስማት ጀምረዋል አሉ። የታደሉ እየሳቁ ይሰራሉ። የኔ ሙከራ በፍጹም የፖለቲካ ዘፈን ለመጋበዝ አይደለም። የሙዚቃ ስልቱንም አልችልበት። ለፖለቲካ እስክስታ ሲመቱ ከዐይን ያውጣችሁ የተባሉ አሉና ስራ ለሰሪው ብያለሁ። እትብቴ የተቀበረባት ሀገሬ ኢትዮጵያ ግን ሠርጓ ሠርጌ ሞቷ ሞቴ ነው። መቼስ ለእናት ሀገር “ያገባሽስ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ” አይባልም!
“ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ” አሉ እቴጌ ጣይቱ! ይህች ኢቲቪ የምታሳየን ደጋፊውን ብቻ ስለሆነ ጫወታው ፍዝዝ ብሏል። “ያልታደለች ወፍ ዐይኗ በጥቅምት ይጠፋል” እንዲሉ እኛም አልታደልን ዐይናችንና ኢቲቪ ከተጣሉ ቆይተዋል። ሞቅ ደመቅ ካለው ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ እንግሊዝን ፓርላማ እንመለስ። የእንግሊዙን ፓርላማ ስናይ እርስ በእርሳቸው እንደ ጉድ ይከራከራሉ፣ እንደ ጉድ ደጋፊና ተቃዋሚ ይፋለማሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደ ጉድ ቁጭ ብድግ እያደረጉ በጥያቄ ያፋጥጣሉ፤ አልፎ አልፎ ሳቅ ፈገግ የሚያስብል ቃላትን ወርወር ያደርጋሉ! የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ እና የእንግሊዝን ፓርላማ ያየ ይዝናናል የሚባለውም ለዚሁ ነው። እኛ ቤት ግን ይህ ፍጹም ነውር ነው። ደጋፊ በሀገር ውስጥ ተቃዋሚ በአሜሪካ ሆነው በሁለቱም በኩል ምርጥ ምርጥ የተጋነኑ ዜናዎችን ስንሰማ ዐይናችንም ጆሯችንም ሰልችተዋል።
“ጅብ እንኳን ጓደኛውን ይጠራል” አሉ እቴጌ ጣይቱ። ጅብ በለስ ሲቀናው ድምጹን ከፍ አድርጎ ሌሎችን ጅብ ይጠራል። ይህን የመሰለ እንስሳ ሆዳም ማለታችን እጅጉን ይገርማል። እባካችሁ ተለያይቶ መናከስን ሳይሆን እንደ ጅብ ተጠራርቶ መብላትን ለሀገር መስራትን አስተምሩን። እንግሊዛዊያን ስለ ውድ ሀገራቸው ስለ ታላቅዋ ብሪታንያ አንድ አባባል አላቸው። “አንድ ላይ መስጠም ሳይሆን አንድ ላይ መዋኘት አለብን” ይላሉ። እባካችሁ ለእናት ሀገር ስትሉ አንድ ላይ ዋኙ። እባካችሁ ለእናት ሀገር ስትሉ የሐሳብ ፍልሚያ አሳዩን። የልብ ሳይደርስ እድሜ ይደርስ አሉ እቴጌ ጣይቱ።
የማንችስተርና የአርሴናል ልዩነት ጫወታውን ሞቅ ደመቅ ያደርገዋል። ሁሉም የማንችስተር ደጋፊ ቢሆን የኳስ ውበቱ በጠፋ ነበር። ሁሉም የአርሴናል ተቃዋሚ ቢሆን ኳስ ውበትዋን አጥታ መልከ ጥፉ በሆነች ነበር። የኛ ቤት ጫወታ ግን ፈዘዘ። ኢቲቪ የምታሳየን ደጋፊውን ብቻ ስለሆነ ጫወታው ፍዝዝ ቅዝዝ ብሏል። አፈር ስሆን አሁን ማን ይሙት የእንግሊዝ ቻናሎች ቢሆኑ ያ ሁሉ “ዕንባ አዋጡ” የሚል ፕሮግራም የሚተላለፍ ይመስላችኋል? መልሱን ለኢቲቪ ትቻለሁ።
“ሳያርፉ ዐረፉ”
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ላይኛው ሀገር ሄደዋልና የሞተን መውቀስ ለሕሊናም አይመችም። ነፍስ ይማር ማለት ሰዋዊነት ሰብአዊነት ኢትዮጵያዊነት ነው። አንድም ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው። ነፍስ ይማርና በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ 19 ዓመቴ ጀምሮ እረፍት የሚባል ነገር አላየሁምና በሀገሬ ሆኜ የትርፍ ስራ እየሰራሁ ማረፍ እፈልጋለሁ ብለው ነበር። ይህ ቢሳካ ኖሮ ሀገሬ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ጎዳና ዳዴ ማለትዋ በታወቀ ነበር። ምኞታቸው አልተሳካምና ስልጣን በፈቃዱ የለቀቀ ጀግና ሀገሬ እንዳማራት ጎምጅታ እንዳማራት ትቀራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጊዜ እጥረት የተነሳ ማንበብ እየፈለኩ ያላነበብኩት መጻፍ እየፈለኩ ያልጻፍኩት ነገሮች አሉ፤ ወደ ፊት ምን እንደሚሆን አይታወቅምና ከስር ከስሩ ማየት እፈልጋለሁ ብለው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ሞት ቀጠሮ ይዞ ኖሯል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳያስቡት ድንገት የቤተመንግስቱን በር አንኳኩቶ መጣ። የናፈቁትን ረፍት ሳያዩ ዐረፉ። “ሳያርፉ ዐረፉ”
እቴጌ ጣይቱን መለስ ዜናዊ “ሳያርፉ ዐረፉ” ስላቸው ነፍስ ይማር አሉ። ዜና እንዴት ነበር? አልኳቸው ኢቲቪ እንደማይዋጥላቸው ስለማውቅ። አዬ እንደ ስራቸው አሉ እንደለመዱት። እቴጌ ጣይቱ እገሌ እንዲህ ሆነ ሲባሉ “እንደ ስራው” ማለት ይቀናቸዋል። ምንም ይሁን ምንም ወሬ በሰሙ ቁጥር “እንደ ስራው” ይሉ ነበር። ትልቅ አባባል ነው። የሆነው ይሁንና ኢቲቪ የምንከፍተው ግን ምን እንደሚተላለፍ እርግጠኛ ሆነን ነው! “ዕንባ አዋጡ!” የሚል ዜና ለማየት እንደሆነ እኛ ሳንሆን ቴሌቭዥኑም አሳምሮ ያውቃል!!
“ዕንባ አዋጡ!”
~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~
የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!!
No comments:
Post a Comment