Friday, 30 November 2012

“ፍቅር እስከ መቃብር”


“የማትወድህን ሰው ማፍቀር ማለት ኤርፖርት ሄዶ መርከብ መጠበቅ ማለት ነው!” ከዕለታት ፩ድ ቀን ፪ ፍቅረኛሞች በጣም ይዋደዱና “ፍቅር እስከ መቃብር” የሚለውን ታሪክ እውን ለማድረግ ከ፩ድ ትልቅ ገደል ጫፍ ላይ እራሳቸውን ወርውረው በአንዴ ሰጥ ረጭ ሙትት ለማለት ይስማማሉ። ከዚያ ከገደሉ ጫፍ ላይ ሆነው ማን ይዝለል? ማን ይዝለል? እየተባባሉ ሲገባበዙ ሁለቱም ዐይናቸውን ጨፍነው እስከ ሦስት ቆጥረው እኩል ለመዝለል ተስማሙ። ከዚያ ወንዱ ጮኽ አለና ፩ ፪ ፫ ብሎ ቆጠረና ዘሎ ከገደሉ እራሱን ሲወረውር ሴቷ በቆራጣ አየት አድርጋ…….“ህም እውነትም ፍቅር እውር ነው ወይ መቅበጥ!” ብላ ወደ ቤትዋ ትሄዳለች። ወንዱም ወደ ላይ አንጋጦ ሲመለከት ፍቅረኛውን ያጣታል። ለካስ ፓራሹት በጃኬቱ ደብቆ ይዞ ኖሯል ፓራሹቱን ወዲያው ከፍቶ እየተምዘገዘገ የአየር ላይ ግጥም ነጠላ ዜማውን እንዲህ ብሎ በአየር ላይ ለቀቀ



ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው
ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው
ከደንጊያ ይበልጣል ለተሸከመው ሰው

ወይ ፍቅር ሰው ሁሉ ያወራል
ግን ማንም አላየው ቆሞ ሲሄድ በአካል

የሚለውን የራሱን ዘፈን እየኮመኮመ በሰላም ወርዶ ከገደሉ ስር ካለው ሜዳ ላይ ሄዶ ዘጭ አለ!

ድንቄም ፍቅር እስከ መቃብር! ይህን ታሪክ ያየ ጭንቅላት እኔ ነኝ ያለ ፍልጥ ይዞ መጣና ለልብ እንዲህ አለው፦ ፍሬንድ ሁለተኛ ታፈቅርና ውርድ ከራሴ!” ብሎ ፎከረበት አሉ። መቼስ አሉ ነው። ልብም በተራው ለፍሬንድ ጭንቅላት እንዲህ አለው፦ ፍሬንዴ አሪፍ አፍቃሪ ካገኘሁ ፍቅር በፍቅር እንሆናለንኮ ብሎ ተስፋ ሰጥቶታል አሉ። እኔ የምላችሁ የአንተ ወይም የአንቺ ልብና አእምሮ እንዲህ ተፋጠው ያውቃሉ እንዴ? “ልፋ ያለው በህልሙ ክብደት ይሸከማል” እንዲሉ አንዳንዱ “False dream” ወይም በተሳሳተ ህልም ሲቃዥ አድሮ “ትዳር ማለት ምድራዊ ገነት ነው የሚል አለ። ያ ደግሞ ትልቅ ስህተት ነው። ይህ ደግሞ የትዳር ፍቺ ምክንያት ነው። ከመቻቻል በፊት ከትዕግስት በፊት ዘሎ ሩጦ መፋታት ደግሞ ከፈረሱ በፊት ጋሪው ቀደመ ያስብላል።




አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሽማግሌ ሳይጋቡ የተፋቱ ባልና ሚስትን ለማስታረቅ ለሽምግልና ተጠርተው ምን አሉ መሰላችሁ? “አንበሳ ሲያረጅ የፈረንጅ መጫወቻ ይሆናል” አሉ። ሁላችንም እድሜ ተጫጭኗቸው ስለ እድሜ ዕርግናቸው የሚያወሩ መስሎን ነበር። ግና ሽማግሌው አቶ ዘካርያስ ቅኔ ነበር የተናገሩት። እነሆ ታሪኩ እንዲህ ነው፦


አንዳንዶች ፍቅራቸውን ሲገልጹ Honey sweet I LOVE YOU እያሉ ለዚህች ጊዜ ብለው የተበደሯትን እንግሊዘኛ ጣ’ል እያደረጉ የፍቅር አ-ቦ-ጊ-ዳ ሳይሆን በአውሮፓ ፍቅር እልም ብለው ይጠፋሉ። ሳምንት ሳይሞላ በእንግሊዘኛ እንደተዋደዱ በእንግሊዘኛ መጣላት ያምራቸዋል። ይህ ነው ሳይጋቡ ተፋቱ የሚባለውን ትዳር ያመጣው። አልሰሜን ግባ በለው አሉ። አልሰማችሁም እንዴ? “ሳይጋቡ ተፋቱ” የሚባል ትዳር አለኮ። ፍቅር እስከ መቃብርማ ድሮ ቀረኮ። ዛሬማ ፍቅራችን ፈረንጅኛ ሆኖ የተጣሉ ባልና ሚስትን የሀገር ሽማግሌ ሊያስታርቅ ቢሞክር የማይፈታ ህልም ሆኗል። እናላችሁ ሽማግሌው የተጠሩበት ሽምግልናም በእንግሊዘኛ ተፋቅረው በእንግሊዘኛ የተጣሉ ባልና ሚስት ነበሩ፤ ለዚህ ነበር ሽማግሌው “አንበሳ ሲያረጅ የፈረንጅ መጫወቻ ይሆናል” ያሉት። በሽማግሌው ዘመን የነበረው ፍቅር አርጅቶ ዛሬ የፈረንጅ መጫወቻ ስንሆን እውነትም “አንበሳ ሲያረጅ የፈረንጅ መጫወቻ ይሆናል” ያስብላል!! በመጨረሻም ሽማግሌው ዘካርያስ የባልና ሚስቱን የውስጥ ፍቅር አይተው “ፍቅርና ጉንፋን አይደበቅም” አሉና የተኳረፉትን ባልና ሚስት አስታረቁ።


ሽማግሌው ዘካርያስ የዘመናቸውን የፍቅር ጊዜያት በእግረ ሕሊናቸው ሄዱና እንዲህ ብለው ታሪካቸውን አወጉን። በኛ የፍቅር ግዜማ የፍቅር ጥያቄው ለጉድ ነበር። የወደድናትን ልጅ በቅኔ ነበር የምንነግራት። እስኪ የኔን ታሪክ ልንገራችሁ” ሲሉ ሁላችንም ሰፍ አልን። ስለ ፍቅር ሲነሳ ወጣቱ መንሰፍሰፉን (መንሰፍሰፋችንን) አይተው ሽማግሌው ፍግግ አሉና ታሪካቸውን እንዲህ ብለው ቀጠሉ። ያኔማ አሉ ሽማግሌው ፅህማቸውን እንደ ጉድ እየዠረገጉ። ያኔማ ባለቤቴ የልቤነሽ ገና ከሩቅ ሳያት ልቤ ክው ነበር ያለው። ለዚህ ነው የልቤነሽ” ብዬ የምጠራት። እናማ ወደኔ ቀረብ ስትል ምን አልኳት መሰላችሁ? “ልብ ካላየ ዐይን አያይም ሲባል አልሰማሽም? ልቤ አየሽና ለዐይኔ ነገረው። ዐይኔም ለልቤ ይህችን ልጅ ውደዳት አለው” ብዬ ግጥም ደረደግኩላት። የልቤነሽም ኩራትዋ ለጉድ ነበርና በስንት መከራ okay አለችኝ። [ይህን ጊዜ ሁላችንም ፍግግ አልን] ሽማግሌው ወጋቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ…….. “ሴቶች ሆይ ከፕላኔት የወረደ ወንድ ስትጠብቁ እንደ አክሱም ሐውልት ቆማችሁ እንዳትቀሩ ተጠንቀቁ! ሴት ወንድ ለተባለ መኪና ሞተሩ ናት! ወንዶች ሆይ የቆመ መኪና እንዳትሆኑ የሀገራችሁን ሸበላ መላ መላ በሉ” ብለው ሽማግሌው ለወጣቱ መልዕክታቸውን ለግሰዋል። አቶ ዘካርያስና ወ/ሮ የልቤነሽ ገና በፅንስ እያሉ ነበር በወላጆቻቸው ልጅህን ለልጄ” ተባብለው የታጩት። ፍቅር ከፅንስ እስከ ሞት ይልሃል ይህ ነው! ሽማግሌው አቶ ዘካርያስ ከተወደዱ ባለቤታቸው ከወ/ሮ የልቤነሽ በተባረከው ትዳራቸው ፫ ወንድና ፮ ሴት ልጅ ወልደዋል።


ይህ የአባ ወራ እና የእማ ወራ ፍቅር እስከ መቃብር ነው። ዛሬ ዛሬ ፍቅር እስከ መቃብር ሳይሆን ፍቅር እስከ ጳጉሜ የተባለ ይመስል የአምስት ቀናት ፍቅር እናያለን። በአንድ ወቅት በአንድ አጋጣሚ ልባቸው ክፉኛ የተሰበረ ሰዎች ጭንቅላታቸውን ይዘው…… ውይ ወንዶች ስትባሉ ልብ አቃጣይ ናችሁ! ውይ ሴቶች ስትባሉ እባብ ናችሁ! ወንድን ያመነና ጉም የዘገነ አንድ ነዉ "ገንዘብ ዛፍ ላይ ቢበቅል ኖሮ ሴት ልጅ ጦጣ ታፈቅር ነበር" ወዘተ ተረፈዎችን  የሚሉ ሞልተዋል። “ከኑግ ጋ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ ያገኙትን ሁሉ ወንዱንም ሴቱንም በጅምላ መውቀጥ ግን እኔ ልሙት እላችኋለሁ ልክ አይደለም። ኑግና ሰሊጡ መለየት አለበት። ሁሉም ታማኝ እንዳልሆነ ሁሉ ሁሉም አታላይ አይደለምና። ባለፈው የፍቅር ዘመን የቆሰለ ልብ ዘንድሮም ምን አልባት ከቆሰልኩ እያለ የሚፈራ ቢኖር ባለፈው ዝናብ ዘንድሮ አይታረስም” ብዬዋለሁ። አልበርት አነስታይን እንዳለው “ሕይወት እንደ ሳይክል ናት፤ ባላንሱን ለመጠበቅ የግድ መጓዝ ያስፈልጋል!” ብሏል። ስንጓዝ ግን የፍቅር መንገዱን እያስተዋልን መሆን አለበት፤ ስትሄድ የመታህ ደንጊያ ስትመለስ ከመታህ ደንጊያዩ እሱ ሳይሆን አንተ ነህ የሚል አባባል አለና!

አንዱ ብረት በመግፋት  የጠበደለ ወዳጄ “ከክብደት እና ከትዳር የቱ ይከብድ ይሆን?” ብሎኛል። አንዷ ወዳጄ ደግሞ ልቤ ፍቅርን ባከበረ ቅስሜ ተሰበረ” ብላ ታሪኳን ዘክዝካ ነግራኝ ነበር። በታሪኳ ልቤ ተሰበረ። ፍቅር ማለት በሁለት ሰው ጣት እንደተወጠረ የብር ላስቲክ ነው፤ አንደኛው ቢለቀው ሌላኛው ይጎዳል። እነሆ ልብ ያለው ልብ ይበል ጆሮም ያለው ይስማ! መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” ይህ ያጋጠማችሁ ፍሬንዶቼ የፍቅር ጉደኛ ሳይሆን የፍቅር ጓደኛ ይስጣችሁ፤ አሪፍ አፍቃሪ አግኝታችሁ ፍቅር እስከ መቃብር ያድርግላችሁ ብዬ ተመኝቼያለሁ።

የአንዳንዱ ሰው ፍቅር ልክ እንደ እንግሊዝ ዛፍ ነው። የእንግሊዝ ዛፍ ፀሐይ በሚሆንበት ጊዜ ቅጠሉ ለምልሞ አበባው ፈክቶ ይታያል። የክፋትዋ ክፋት ፀሐይዋ ደግሞ ለሁለት ወር ብቻ ነው ብቅ ብላ የምትጠፋው። ፀሐይዋ ስትጠልቅ ቅጠሎችም ይረግፋሉ። የገና በረዶ ሲመጣ የዛፎቹ ቅጠሎች ረግፈው እነሆ እንጨት ብቻ ይቀራል። ልክ እንደ እንግሊዝ ዛፍ ጊዜው ሲመቸው ብቻ ቅጠሎቹ አብበው ፍቅራቸው ደርቶ ቤታቸው ገነት የሚመስሉ ሰዎች አሉ። በችግር ጊዜ ፀሐይዋ ስትጠልቅ ደግሞ ቅጠሎቹ ረግፈው ፍቅራቸው እንጨት እንጨት የሚላቸው ሰዎች ሞልተዋል። በባል ወይም በሚስት መካንነት ልጅ በመሃል ሲታጣ አበባ የነበረው ፍቅራቸው ደርቆ እንጨቱ ብቻ ይቀራል። ይህን ጊዜ ሚስት ባልዋን “ፍሬ ቢስ” ትላለች። ባል ደግሞ ሚስቱን ፍሬ የሌላት እንጨት ብቻ ናት” ይላል።


“የባል ኑዛዜ”

ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና “እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል። ኑዛዜ ይልሃል ይህ ነው! ከእንዲህ አይነቱ ኑዛዜ ይሰውራችሁ ይሰውረን  አሜን አሜን በሉ።

አሁን እስኪ በሞቴ ዘና ብላችሁ ተቀመጡና ሻይም ሆነ ቡና ፉት እያላችሁ ይህችን ታሪክ ተጋበዙልኝ፤ ብልጥ አውራ ዶሮ በሰው ብቅል ሚስቱን ይጋብዛል አሉ!!


==>የፍቅር ዓይነቶች”<==

ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት!” አንዲት የሰፈር ጓደኛዬ ፀጉሯን ምን ውስጥ እንደምትነክረው አላውቅም ብቻ ዘመናዊ ነኝ ለማለት እንደ ቀስተደመና በየቀኑ የፀጉሯን ቀለም ትቀያይረዋለች፤ ሰኞን ስለማትወደው ጥቁር ቀለም፣ ማክሰኞን አረንጓዴ፣ እሑድን ሰማያዊ ቀለም እያለች ትዘምንብን ጀመር። የማይቆረጡ ፀጉሮች አያድጉም ፀጉር ያድጋል ፋሽን ያልፋል የሚል መፈክርም አላት። እናላችሁ ከፀጉር ቀለሟ ጋ የሚሄድ ጥብቅብቅ ያለ ሱሪ ትለብስና ጫማዋዋን ትጫማና ከላይ የልጅነቷ የሚመስለውን ጃኬት ጣ’ል ታደርግና በቃ! ከተሜውን ታዳርሳለች!

እቴጌ ጣይቱም የሰፈራችን የአቶቢስ ተራ እማ ወራዎችን ሰብስበው እንዲህ የሚል ግጥም ገጠሙላት፦

አየን አወራነው የፀጉርሽን ነገር
ትንሿን ኮትሽን ለትንሿ ልጄ ብትሰጪያት ትፀድቂ እኮ ነበር!
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
ይህች አንዲት ፍሬ ልጅ በፈረንጅ ተገዝታ ትዝናናብን ወይ!


ከዚህች የልጅነት አብሮ አደጌ ጋ አፈር ፈጭተን ውኃ ተራጭተን ነውና ያደግነው የሆድ የሆዳችንን ሳንደባበቅ እንጨዋወት ነበር። እሺ…… ግጥም ተገጠመልሽ አሉ! አልኳት ነገር ፈልጌ። ይኹና! አለች አንገቷን ሰበቅ አድርጋ። ለምን እንዲህ እንደምሆን ታውቃላችሁ? አለች እያፈጠጠችብኝ። ኧረ አናውቅም አልኳት ወደ ኋላዬ እያፈገፈኩ። ለምን መሰለህ? እኔ ፍቅር ይዞኛል! በቃ ልሙት እንዴ? አለችና የፍቅር ዕንባዋን አወረደችው! አለቀሰች። ከቦርሳዋ ውስጥም ወደድኩት ያለችውን ሰው ፎቶውን አሳየችኝ። ወዲያው በአንድ መፅሐፍ ውስጥ የልጁን ፎቶ አድርጋ ሰጠችኝ። እኔም በጣም ከረጅም ጊዜ በኋላ ያንን መፅሐፍ ዛሬ ከልብሴ ሻንጣ ውስጥ አገኘሁትና በማስታወሻዬ ላይ ጻፍኩት! የልጅነት ጉደኛዬ የሰጠችኝ መፅሐፍ ርዕሱ የፍቅር ዓይነቶች የሚል ነበር።

የፍቅር ዓይነቶች” (types of Love)

/1/ “ሮማንቲክ ላቭ” /Romantic Love/

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ሄሮድስ ነው። ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ያፈቀራት ስትደንስ አይቷትና ዳንሷም ስለማረከው ብቻ ነው። ይህ ዓይነቱ ፍቅር “ሄሮድሳዊ ፍቅር” ይባላል። ይሄኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርጽ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው። ሌሎች መሰረታዊ ነገሮችን ለምሳሌ ሃይማኖት ፣ ባሕርይ ፣ አስተሳሰብ ወዘተ ተረፈዎችን ከቁም ነገር አይቆጥሩትም። ሮማንቲክ አፍቃሪዎች ብዙን ጊዜ ቀናተኛ ናቸው። ያፈቀሩት ሰው ከማንኛውም ሰው ጋ እንዲያዩት አይፈልጉም።

/2/ “ፓሽኔት ላቭ” passionate Love

ስሜታዊ ፍቅር! ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር ነው። ስሜታዊ ፍቅር passionate Love በጣም አስቸጋሪ የፍቅር አይነት ነው። ሕሊናን ረፍት ከመንሳቱ በላይ ሕይወትን የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ አለው። ለምሳሌ ትምርትና ስራ መጥላት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ይገኙበታል። ስሜታዊ ፍቅር የሚቆየው ስሜቱ እስኪሳካ ሩካቤ ሥጋ እስኪፈፅም ድረስ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ግን መጀመሪያ ከወደደው ውድ ይልቅ በኋላ የሚጠላው ጥል ይበልጣል! ይህን የመሰለው ፍቅር በመፅሐፍ ቅዱስ የአምኖን ፍቅር /አምኖናዊ ፍቅር/ ይባላል።


/3/ “ሎጂካል ላቭ” Logical Love

ይህ ፍቅር ጣራና መሰረቱ “መመሳሰል” የሚለው ቃል ነው። እነዚህ ፍቅረኛሞች የሚመሩት በሎጂክ ነው። ለምሳሌ እሷ ድግሪ ካላት የምትመርጠው ድግሪ ያለውን ሰው ነው። ወንዱም እንደዚሁ።


/4/ “ፍሬንድ ሺፕ” /Casual friendship/

ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም። ሁለቱ ፍቅረኛሞች ምስጢር ይለዋወጣሉ፣ የሚያስደስታቸውም ጥምረታቸው ብቻ ነው።

/5/ “ፉሊሽ ላቭ” foolish Love

“የጅል ፍቅር” አንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው። ለምሳሌ ምንነቱን ሳታውቅ ፎቶውን ብቻ አይታ ከነፍኩ በረርኩ የምትል ሴት አጋጥሟችሁ አያውቅም? ፎቶውን ብቻ አይታ ወደደችው! በቃ! ቆረጠች። በእቴጌ ጣይቱ ጥናት መሰረት ብዙዎች በዚህ ፍቅር ከተያዙ ቆይተዋል ይባላል። እድሜና ጤና ለፌስ ቡክ ይሁንና የእቴጌ ጣይቱ ጥናት ፍንትው ብሎ ያሳየናል። ይህ አይነቱ ፍቅር በምሁራን አገላለፅ “የጅል ፍቅር” foolish Love ይባላል።

/6/ “ፖሰሲቭ ላቭ” /possessive Love/

ይህ ዓይነቱ ደግሞ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ነው። ወንድ ስለሆንክ ለራስህ አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ጥናቱ እንደሚያሳየው ብዙውን ጊዜ ይህ አይነት ፍቅር የሚይዛቸው ሴቶች ናቸው። እንደዚህ ዓይነቶቹ የእገሌ ባል መባልን ይፈልጋሉ። 
/7/ “አንሰልፊሽ ላቭ” unselfish Love

ይህ እሷ ከምትጎዳ እኔው ልቸገር ዓይነት ፍቅር ነው። ፍቅር ግን መዋደድ እንጂ ውለታ መዋዋል አይደለም።

/8/ “ጌም ፕሌይንግ ላቭ” Game playing Love

ይህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ዓላማቸው አንድ ብቻ ነው። የሩካቤ ሥጋ ጥማቸውን ማርካት ብቻ። ይህ ብዙውን ጊዜ በወንዶች የሚበረታ የፍቅር ዓይነት ነው።

/9/ “ኢምፒቲ ላቭ” Empty Love

ባዶ ፍቅር! ይህ ዓይነቱ ፍቅር በአጋጣሚ ተገናይተው ወደድኩሽ ፣ ከነፍኩልሽ ፣ አበድኩልህ ፣ ክንፍንፍ አልኩልህ የሚያሰኘው ነው።

/10/ “ሰልፊሽ ላቭ” selfish Love

ራስ ወዳድ ፍቅር! እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርን ሀ” ብለው የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ነው። ለዚህኛው ፍቅር መሰረቱ ገንዘብ ነው። “ገንዘብ ያልቃል ፍቅር ግን ይዘልቃል!ገንዘቡ እስካለ ድረስ ሆዴ! አንጀቴ! ሞትኩልህ! አበድኩልሽ! ይባባላሉ። ገንዘቡ የጠፋ ዕለትስ? ያኔማ ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ ዓይናቸውንም አያሹም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን የኢዮብ ሚስት ናት። ኢዮብ ሐብት ንብረቱ ሲያልቅ የሚስቱ ፍቅርም አለቀ፤ ኧረ እንዲያው ለመሆኑ ፍቅር በአንድ ጊዜ የሚለቅ የጥፍር ቀለም ነው እንዴ? ይህ ዓይነቱ ፍቅር ገንዘቡ ሲጠፋ ፍቅሩም ድርግም የሚል የኢዮባዊ ሚስት ፍቅር” ይባላል።

/11/ “ኮምፓኒየን ላቭ companion Love

ይህ እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጪ ወጣ ያለባቸው ሰዎች የሚጀምሩት ውጥን ነው። ከእድሜያቸው ጋር ግብግብ ስለሚይዙ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ያገባሉ። ምክንያቱም ፊታቸው ያለው የልጅ አምሮት ፣ ልጅ ማሳደግ አብሮ መኖር …… ነው። እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ ትዳራዊ ፍቅር companion Love ይባላል።


/12/ ፍቅር …. እስከ …. መቃብር “ኮንሲዮሜት ላቭ consummate Love

ይህ ዘለቄታ ያለው የአባ ወራ እና የእማ ወራዎቻችን ፍቅር ነው።  ይህ ክቡር አዲስ አለማየው እንደደረሱት “ፍቅር እስከ መቃብር” እንደ በዛብህና ሰብለ ወንጌል ያለ ፍቅር ነው። ይህ የሽማግሌው የአቶ ዘካርያስ እና የወ/ሮ ልቤነሽ “ፍቅር እስከ መቃብር” ነው! ይህ “እውነተኛ ፍቅር ነው!!


ፍቅርን ፍቅር ነው የሚያሰኙት 3 ነገሮች ሲሟሉ ነው።

ስሜት /passion/
ቅርበት /intimacy/
ቁርጠኝነት Commitment  

መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” እንዲሉ መግባባት ያስፈልጋል። ሁለቱ ፍቅረኛሞች በስሜትና በአስተሳሰብ መግባባት አለባቸው። በአስተሳሰብ መቀራረብ ያስፈልጋል። በችግርና በኀዘን ለመረዳዳት ቁርጠኝነትም ያስፈልጋል።ራስን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ማንም ራሱን ፈልጎ ማግኘት አለበት! እኛ የቱ ጋ ነው ያለነው?


*********

ይህችን ፅሑፍ ከጨረስኩ በኋላ ወዲያው የልጅነቴን ጓደኛ ደወልኩላት።ሔርሜላዬ እንደምን አለሽ? አልኳት ተጣድፌ። ሰላም ነኝ አለች….. በቃ የሆድ የሆዳችንን ተጨዋወትን። የሰጠሽኝን መፅሐፍ በድጋሚ ሳነበው ትዝ ብለሽኝ ደወልኩልሽ፤ አሁንም ፍቅር እንደያዘሽ ነው? አልኳት ድሮ እንደምቀልድባት ፍግግ እያልኩ።

የሰጠውህን ፎቶህንስ ጣልከው እንዴ?” አለችኝ።

ከላይ ሳልነግራችሁ፤ ለካ ወደዱኩት ብላ የሰጠችኝ የራሴን ፎቶ ነበር!

“እንዴታ አለ አልጣልኩትም” አልኳት።

ሔርሜላዬ ከ2 ወር በኋላ እንደምታገባና በሠርጓ ላይ መገኘት እንዳለብኝ ነገረችኝ። በደስታ እንደምገኝ ነገርኳት። ጓደኛዬን ይዜ መምጣት እችላለሁ? ስላት “ለጓደኛህ ቦታ የለንም” አለች ድሮ እንደምትጫወትብኝ እየቀለደችብኝ። ጓደኛ ስለመያዜም ወተወተችኝ፤ ማን ናት ወዴት ናት ….. አይ አብሮ ማደግ! ታላቅ ነው ለካ!


……. አይነጋ የለ ነጋ ጊዜውም ነጎደ……. ያለንበት ወቅት የሠርግ ጊዜ ነው……. ለታላቅዋ የልጅነት ጓደኛዬ ታላቅ ስጦታ መያዝ አለብኝ……. ግን ምን? ታላቁ ስጦታዬ የዛሬ 11 ዓመት ሔርሜላ የሰጠችኝ የፍቅር ዓይነቶች” የሚለው መጽሐፍ ነው። አሁን ይህችን ውድ ስጦታ ይዤ ወደ ሠርጉ መገሥገሥ አለብኝ።


ለምወዳት የልጅነት ጓደኛዬ ለሔርሜላዬ ትዳርዋ ፍቅር እስከ መቃብር ይሁንላት።

ለተጋባችሁ ፣ ለመጋባት ያሰባችሁ ፣ በመጋባት ላይ ያላችሁ ሁሉ ፍቅራችሁ ፍቅር እስከ መቃብር ይሁልናችሁ! አሜን ይሁንልን!


ፍቅር …. እስከ …. መቃብር
========================================================================

©  የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!!                                 
o                                                       
Birhanie Andualem ever best novel
o                                                       
Firewoyne Yimer Ale derasewuu ahune gen eseke gudeguewademe yeleme lol
o                                                       
Tibebe Gebresilassie Zewge dero neberh fekerh ahune gen fekerh birr unwale
o                                                       
Samuker Hussen behon des yelal
o                                                       
Roman Kassahun Befesum fikere bemedere laye yelem Andun setewede yewededekew lela sewede yewededat lela setewede yewededechiw lela sewed endehe honal medere. laye ye fikere megetatem tefeto yalewen teto yesew eyetemege zelalem Alemachinene enenoralen enay yemelew ye egzehabehare kuta new geta ewenetega fikere kewesetachin yefeterelen Amem Amen Amen
o                                                       
Embete Dagne Emu Teru love is 1 god.......... Fkr e/r becha mahonune naw yemisemamawe eny
o                                                       
Beza Hayleleoul Yoni enem eskahun fekrena yalyazkut fker eske mekabr bewnetaw afkari yehonech sefelg new
o                                                       
Mhret Tse Woooowwww betam des yemil tarik ena tmhrt new wendm yonas enamesgnalen !!!!!
o                                                       
Martela Lulu wow wow wow anebebekute lebe esekitefa yemimesete tarike nwu bezu negere enedawuke aderegehegnale lekase yeheme ale enede enede fetari edemehene yarezemelegne God Bless U Yonas
o                                                       
Yordanos Melis amen my dear
o                                                       
Etagegn Teju fiker yetagesal,chernetnm yadergal,aykenam,aymekam,aytabeyim,yemaygebawen ayadergm,yerasun ayfelgm,aybesachm,bedeln aykotrm,ke ewnet gar des yelewal enji sileametse des aylewm,hulun yetagesal,hulun yamenal,hulun yamenal,hulun tesfa yadergal, behulu yetesenal, neber yemelew YEGEZIYABHER kal gn erasachnen sinay andun enkuan metegber alchalnm ....fikr yisten amen.....lol
o                                                       
Rahel G Gebre Betam aznajna astemari tarik new, enamesegnalen!!!
o                                                       
Tigest Bayou betam des yemil tarik new enamesgnalen!!!!!!!!!!!!!!
o                                                       
Mente Wazza Utd GBU yoni
o                                                       
Etaferahu Woled Amen gbu
o                                                       
Misiker Degu Ya betam das yamel tekes new 10.Q
o                                                       
Eyerusalem Tilahun Wow......wow......wow....
o                                                       
Selamawit Mekonnen wow yemigerme new tnx yoni
o                                                       
Orange Chuchu Crown Betam des ylal 10q yonas
o                                                       
Sintayehu Sisay wow Lij yonas endet bemamir leza agerbkew meslek yekidame chawtakin,,,,,,tebarekilin amen!!!
o                                                       
Fekadu Girma Lehulachinm asteway libuna yisten! Yonni 10q
o                                                       
o                                                       
Abebe Getachew Seblewengel Meshesha+ Bezabih Mebratu
o                                                       
Selam Dechasa wow betam des yemel azenagne ena asetemar tarek new
o                                                       
Roman Wuebet Church bewnte betame dese yemlree naw gene eskze yetne naw nabrke ? baselame kewene melkame naw
o                                                       
Biruk Fikadu ohhhhhhhhhhhhhhhhh asedemami yehone tarik
o                                                       
o                                                       
Alemtsehay Akalu Wow! Bizu kumneger astemarken,tnxs alot!!
o                                                       
Tg Negash eshy eyetebekn new
o                                                       
Hailu Chala waw egzeiabhar yebarkehe menem malat alchelem berta tebarek bezu neger aswekehal wawwww
o                                                       
Getu MuLugeta Wow 100 persent true!!! fekir eske mekaber.
o                                                       
Asmare Birhanu Be ewnetu Yoni yengna ye Fb guadegnochih comedyachin ena astemariachin silehonk sitetefabin betam new midebren selezih ketafach keldochih gar yecenimachinen ye Fb meri adirgenehalena atitefa!
o                                                       
Netsanet Alemayehu Des yemil timihert new bekelid eyawazah yemitakerbachew negeroch hulu des yilalu yeagelgilot zemenihn yibarkilih.
o                                                       
Admas Awek Good idea
o                                                       
Behailu Kassaye metadel new
o                                                       
Selam Sisay oretodoces betame fekere nwe












No comments: