Saturday, 18 February 2012

“ግማደ መስቀሉ ከጎሎጎታ እስከ ግሸን ደብረ ከርቤ”


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በስላጣኑ ከተነሳ በሗላ መስቀሉ ቀን ከማታ ያበራ ነበረ። አይሁድ ቀንተው ቀበሩትና የቆሻሻ መጣያ እንዲሆን አወጁ። 300 ዘመን በሗላ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ከቁስጥንጥኒያ መታ የክርስቶስን መስቀል አስቆፍራ ለማውጣት በጸሎት 7 ቀን ከቆየች በሗላ መላኩ ዑራኤል ተገልጾ ደመራ አስደምረሽ በእሳት አያይዘሽ በዛ ላይ ብዙ እጣን አድርጊ የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወቶ መስቀሉ ያለበትን ቦታ ያሳይሻል አላት። እንዳላትም አድርጋ መስከረም 10 ቀን 370 . ሃይላችን የሆነው መስቀሉ ተገኘ።

መስቀሉ ቀንና ለሊታ ሲያበራ የፋርስ ባቢሎን ንጉስ ወደ ሃገሩ ወሰደው። በዚህም ግዜ የእየሩሳሌም ንጉስ ለሮማው ለንጉስ እርቃን እርዳታ ጠየቀ። የሮማው ንጉስ ዳግመኛ መስቀሉን በሃገሬ አኖራለሁ ብሎ ወደ እየሩሳሌም ዘመተ። በዚህን ግዜ የእየሩሳሌም ንጉስ የፋርስን ንሱስ ረዳት አድርጎ ሲከላከል 4 ክፍላተ አለም የሃይማኖት አባቶች መስቀሉ 4 ተከፍሎ 4 ሃያለን መንግስታት ቢቀመጥ ይሻላል አሉ። የቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀሉ ለአፍሪካ ደረሰ። አፍሪካዊያን ተማክረው ግብጽ እስክንድርያ ገዳም ውስጥ እንዲቀመጥ አደረጉ።


ግማደ መስቀሉ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ

የግብጽ እስላሞች በብዛትና በሃይላቸው ባየሉ ግዜ የእስክንድርያን ክርስቲያኖች አስጨነቁ። አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የሚባሉ ሁለት የግብጽ ጳጳሳትን አሰሩ።
በዚህን ግዜ የግብጽ ክርስቲያኖች በወቅቱ ሃያል ለነበረው ለኢትዮጲያ ንጉስ ከአፄ ዳዊት እርዳታን ጠየቁ። ንጉስ አፄ ዳዊትም መነኮሳትን ባህታዊያንንና ካህናትን ሰብስቦ በጉባኤ ውሳኔ ወሰኑ ሁለቱ ጳጳሳት እንዲፈቱና የግብጽ ክርስቲያኖች የግፍ አገዛዝ እንዲቆም የክርስቶስ መስቀልም ወደ ኢትዮጲያ እንዲመጣ ብለው ታላቁን ጉባኤ ፈጸሙ። ንጉስ አፄ ዳዊት 10 ፈረሰኞች 10 በቅሎ 10 ግመልና በብዙ እግረኞች ታጅበው ወደ ስናር (ካርቱም) ደረሱና መልእክት ወደ ግብጽ ላኩ። የተሰጣቸውን የወርቅ ስጦታ መልሰው ግማደ መስቀሉን ከብዙ ቅዱሳን አጽም ጋር ጠይቀው ተሰጣቸው። በስም አጠራር አንድ የሆኑት ሁለቱ ንጉሶች (ልበ አምላክ ዳዊት አፄ ዳዊት) በተግባርም አንድ የሚያደርጋቸር ስራ አለ ልበ አምላክ ዳዊት ታቦተ ጺዮንን አጅቦ እንደዘመረው ሁሉ ንጉስ አፄ ዳዊትም በእጁ እያጨበጨበ በግምባሩ እየሰገደ ግማደ መስቀሉን ተቀበለ። በእንዲህ እንዳለ ንጉሱ በድንገት ስናር በተባለ ቦታ በቅሎ ረግጧቸው አረፉ። በምትካቸው የኢትዮጲያ ፈላስፋ በመባል የሚያወቁት ንጉስ ዘረያቆብ ነገሱ።  ንጉስ ዘረያቆብ በነገሱ 15 አመታቸው እግዚአብሔር በራዕይ ታያቸውና መስቀሌን በመስቀለኛው አምባ ላይ አድርግ የሚል ራዕይ አዩ።          ንጉስ ዘረያቆብ 3 አመት በጾም በጸሎት መስቀለኛው ቦታ እንዲገለጽለት ጠየቀ።
መላዕኩ ዑራኤል መስቀለኛው ቦታ ግሸን ደብረ ከርቤ እንደሆነ አሳየው፤

ንጉስ ዘረያዕቆብም ግማደ መስቀሉን
በግሸን ደብረ ከርቤ አኖረው።






መስቀል በመፅሐፍ ቅዱስ፦

በእንባ ሆኜ እነግራችሗለሁ; ብዙዎች የመስቀሉ ጠላት ሆነው ይመጣሉ፤ መጨረሻቸው ግን ጥፋት ነው፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለኛ ለምናምነው ግን የእግዚአብሔር ሃይል ነው። ፊሊጵስዩስ 3:18 vs. 1.ቆሮ 1:18

እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች; በፊታችሁ በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳታምኑ ማን አዚም አደረገባችሁ?  ገላ 3:1
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ትምክት ከኔ ይራቅ  ገላ 6:14
በመስቀሉ ባፈሰሰው ደም በምድርና በሰማያት ላሉ ሰላምን አደረገ ቆላ 1:19
ጥልን በመስቀሉ ገደለ ኤፌ 2: 14
ወሥበሐት - ለእግዚአብሔር  [ተክለ መድህን]





5 comments:

Hana wrote: said...

"Amen yoni kale hewot yasemalen Egzyabher yesteln yemetsten merejawoch hulu lehaymanotache tekame nachew ena yoni berta "

Meaza Mulatu said...

Bewnet betam des bilogal Egziabher yistilin kale hiwot yasemalin!!!

wondemagey said...

Thank you Brother!


I appreciate your effort and commitment to feed us with spiritual knowledge and also to be proactive in our religion! I wish you all the best in your life and to be blessed in your Sunday school participation.


keep in touch

ዮናስ ዘካርያስ said...

እስከዛሬ አስተያየት ለምትሰጡኝ አላመሰገንኳችሁምና እስኪ ዛሬ ላመስግናችሁ። ይጠቅማል የምትሉትን ሐሳብ ጻፉልኝ!

Unknown said...

Amen kale hiywot yasemalin bedimena bestega yitebikilin Egzyabher.91