ስለ ፃድቃን ሰማእታት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን መልእክቱ በተከታታይ ምዕራፍ ላይ ይናገራል።
/እብራዊያን ምዕራፍ 11; 12 እና 13/
/እብራዊያን ምዕራፍ 11; 12 እና 13/
+++ እብራዊያን 11:34፦ አለም ለነሱ አልተገባቸውምና በየበረሀው በየዋሻው ተንከራተቱ።
ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ጻድቃን በየበረሃው ተንከራተው እንዳለፉ ነገረን; አሁንም በሀገራችን በየገዳሙና በበረሐው ጤዛ ልሰው ዳዋ ጥሰው ዋእይ ቁሩንም ታግሰው ለሃገር ለህዝብ የሚፀልዩ አበው አሉን። ሃገራችን ብትታረስ ብዙ ጻድቃን የሚበቅሉባት ቅድስት ሃገር ናትና። መናፍቃን ግን ገዳማዊ ህይወትን ይቃወማሉ; ታላቁ ሐዋርያ ግን በመልክቱ አለም ለፃዳቃን እንዳልሆነች ነግሮናል።
+++ እብራዊያን 12:1፦ ብዙ ምስክሮች በዙሪያችን አሉን።
ሐዋርያው ሰማእታትን ምስክሮች አላቸው; ሰማ መሰከረ ሰማእትነት ምስክርነት ማለት ነው።
በእብራዊያን 11:37 ላይ እነ ነብዩ ኢሳያስ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀው ሰማእትነት እንደተቀበሉ ገለጸና እነዚህ ሁሉ ምስክሮች /ሰማእታት/ በዙሪያችን አሉ አለን።
በነፍሳቹ ዝላቹ እንዳትወድቁ የጸናውን አስቡ; እብራዊያን 12:3; ሐዋርያው የጸኑትን ሰማእታትን እንድናስብ ይመክረናል።
እብራዊያን 13:7፦ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፤ የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታቹ በሕይወትቸው ምሰሏቸው።
ብዙ ግዜ የወደቀውን ነው የምንመስለው ነገር ግን የጸኑትን እነ ነብዩ ኢሳያስን እነ አባ ተክለ ሐያማኖትን; ሰማእቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን መምሰል እንዳለብን ይመክረናል።
“ገድለ ሐዋርያት”
ሐዋርያው ቅ/ጴጥሮስ
|
ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቀለ
|
ሐምሌ 5 ቀን 67 ዓ.ም
|
ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ
|
በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ ዐረፈ
|
ሐምሌ 5
|
ሐዋርያው ዩሐንስ
|
በንጉስ ድምጥያኖስ በፍጥሞ ደሴት በፈላ ውሃ በበርሜል ውስጥ ተሰቃየ
|
ሞትን አልቀመሰም
|
ሐዋርያው በርተለሜዎስ
|
ከነህይወቱ አፈር በተሞላ ከረጢት ውስጥ ከተው ወደ ባህር ወረወሩት
|
መስከረም 1
|
ሐዋርያው እንድርያስ
|
በግሪክ ሃገር
በ X መስቀል ላይ ተሠቅሎ ሞተ
|
ታህሳስ 4
|
ሐዋርያው ቶማስ
|
በጆንያ ውስጥ አፈር ሞልተው ጨው ነስንሰው መንገድ ለመንገድ ውሻ እንዲበላው አደረጉት
|
66ዓ:ም
|
ሐዋርያው ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
|
ሄሮድስ አንቲጳስ በሠይፍ አስገደለው
|
በ44 ዓ.ም የሐዋ. 12:2
|
ሐዋርያው ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
|
ከቤተ መቅደስ ጫፍ ወርውረው በድንጋይ ደብድበዉት ዐረፈ
|
የካቲት 10
|
ሐዋርያው ይሁዳ /ታዴዎስ/
|
መጽሐፈ ሄኖክን በመጥቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር 66 ብቻ አለመሆኑን አስረድቷል
|
የይሁዳ መልዕክት ቁ 8
|
ሐዋርያው ናትናኤል /ቀነናዊው ስምኦን
|
በሠይፍ አንገቱ ተቀላ
|
ሰማዕትነት ሲቀበል ሰማይ ተከፍቶ
የሥላሴን ክብር አይቷል ዩሐ. 1:51
|
ሐዋርያው ፊሊጶስ
|
በስቅላት ዐረፈ
|
ከዲያቆን ፊሊጶስ ይለያል የሐዋ 6:5
|
ሐዋርያው ማቴዎስ
|
አንገቱን ተሠይፎ ዐረፈ
|
ኢትዮጲያ መቶ ያስተማረ ሐዋርያ ነው
|
ሐዋርያው ማትያስ
|
በብረት አልጋ አስተኝተው ከስሩ ለ 7 ቀናት ያህል እሣት ለቀቁበት
|
በይሁዳ ምትክ የተተካ ሐዋርያው ነው
|
ወንጌላዊው ሉቃስ
|
በጆንያ አፈር ሞልተው ጨው ነስንሰው ወደ ኤዥያን ባህር ጣሉት
|
ወንጌልና የሐዋርያትን ሥራ ፅፏል
|
ወንጌላዊው ማርቆስ
|
በግብፅ ሃገር ከሠረገላ ጋር አስረው ቀን ሙሉ እየጎተቱት ልብሱ ተቀዶ ስጋውም እንደልብስ ተቆዶ ዐረፈ
|
ሚያዝያ 30
|
ነብዩ ኢሳያስ
|
ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች ብሎ ሲተነብይ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቆ ሰማእትነትን ተቀበለ
|
እብራዊያን 11:34
|
መጥምቁ ዩሐንስ
|
በሔሮድስ አንገቱ በሰይፍ ተቀላ
|
ማቴ 14:10
|
ጲላጦስ ሰማእት
|
ከደሙ ንፁህ ነኝ ብሎ የጌታን ትንሳኤ በመመስከሩ አንገቱን በመሰየፍ ዐረፈ
|
Oxford Christian dictionary
|
ቅ/ፖሊካርፐስ
|
በእሣት ተቃጥሎ ሞተ
|
ራዕ 2:9
|
ቅ/አንቲጳስ
|
በንጉስ ድምጥያኖስ በነሓስ መጥበሻ ተጠብሶ ሞተ
|
ራዕ 2:13
|
ቅ/ሌንጊኖስ
|
አንገቱን ተሠይፎ ዐረፈ
|
የጌታን ጎን በጦር ሲወጋ የጌታ ማየ ገቦ ሲነካው እውር የነበረ አይኑ በራ አናም አመነ
|
አላዛርና እህቶቹ
|
በቀዳዳ መርከብ ጭነው ወደ ባህር ጣሉት
|
በጌታ ትእዛዝ ከሞት ተነስቶ ነበር
|
ሊቀ ዲያቆናት ቅ/እስጢፋኖስ
|
በድንጋይ ተወግሮ ዐረገ
|
ድዳና መስማት የተሳነውን ባገኘ ግዜ እፍ እያለ ይፈውስ ነበር!!!
|
ቅ/ጊዮርጊስ
|
አንገቱን በሠይፍ ተመትሮ ዐረፈ
|
ሚያዝያ 23
|
ኢትዮጲያዊው ጃንደረባ /ባኮስ/
|
ወደ ጋዛ አካባቢ እያስተማረ እያለ በሠማዕትነት ዐረፈ
|
በአለም ለመጀመሪያ ግዜ ጥምቀትን የተጠመቀ ፤ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሐዋርያ ነው!!!
|
ያስቆርቱ ይሁዳ
|
ለዚህ ክብር አልተገባውም
|
ሐዋርያቱ ከአንበሳ ጋር ሲታገሉ ነገሥታቱ እየተዝናኑ የሚያዩበት ስቴዲዮም የሚመስለው ቦታ ይህን ይመስላል
ከሐዋርያቱ አንድም እድሜን ጠግቦ የሞተ የለም፤
እንዲሁ በሰማዕትነት አለፉ እንጂ!
የጻድቃን በረከት ከሃገራችን "ኢትዮጲያና ኤርትራ" አይለይ፤ አሜን!
ወ ሥ በ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
/ተክለ መድህን/