Monday, 20 August 2012

በቤተ-ክርስቲያን ላይ ኳስ ጨዋታ!





ንጉሥ ሱስንዮስ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብሎ ኢትዮጲያ የካቶሊክ ሀገር ናት የሚል አዋጅ አወጀ። በዚህም ዘመን ብዙ ክርስቲያኖች አለቁ። ስምንት ሺህ የሚሆኑ ገበሬዎች ሰማዕትነት አያምልጥህ እያሉ በሱስንዮስ ዐደባባይ አለቁ። ክርስቲያኖች ሰማዕትነት ሲቀበሉ ዲዮቅልጥያኖስ በቤተመንግሥቱ ሠገነት ላይ ሆኖ እንደ ኦሎምፒክ ትርኢት ይመለከት ነበር ይባላል። እንደ ዲዮቅልጥያኖስ የክርስቲያኑን ደም በከንቱ ያፈሰሰው ንጉሥ ሱስንዮስ በነገሠ በሃያ ሰባት ዓመቱ ዲዳ ሆነ። ይህን ጊዜ የንጉሡ ልጅ ፋሲለደስ አባቴ ዲዳ የሆነው በእጁ ደም ስላለበት ነው ብሎ በየገዳሙ በጸሎታችሁ አስቡኝ ማለት ጀመረ። በወቅቱ 
እጅግ ክቡር የነበሩት ባህታዊ አባ አምደ ሥላሴ ሦስት ሱባዔ ይዘው ንጉሡን ፀበል አጠመቁት። ንጉሡም እንደ ካህኑ ዘካርያስ አንደበቱ ተፈታ።

ይህን ጊዜ ንጉሥ ሱስንዮስ “ተዋህዶ ይመለስ ካቶሊክ ይርከስ ፋሲል ይንገሥ” ብለው አዋጁን በአዋጅ ለወጡ። ጊዜውም 1626 ዓ.ም ነበር። እስኪ አሁን ደግሞ ከዚህ ታሪክ አንድ መቶ ዓመታት ወደ ኋላ ዞር ብለን ታሪክን እንጎብኝ። በዓጼ ልብነ-ድንግ እና በግራኝ አህመድ መካከል የነበረውን ጦርነት እናገኛለን። ሊቃውንቱ ከቱርክ በመጣ ሳንጃ እንደ ከብት ታርደዋል። አሁንም ወደ ኋላ ዞር ብለን ታሪክን ስናይ ዮዲት ጉዲትን እናገኛለን። በዚህ የጨለማው ዘመን የማይተኩ ቅርሶች ወድመዋል። ለካስ ወደ ኋላ ዞር ማለት አንገትን ያማል!


እንደምንም ጨክነን አንገታችንን ወደ ኋላ ስናዞር በዚያ ሁሉ የጨለማ ዘመን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ጽሕማቸውን ተነጭተው ለቤተክርስቲያን አንድነት የቆሙ ክቡራን ንዑዳን አበው አሉን። አሁን ችግሩ በስንዴ መሃል እንክርዳድ መብዛቱ ነው። ይህ በቀደሙ አባቶቻችን መስዋዕትነት መቀለድ ነው!! የቀደሙት አባቶቻችን በችግር ውስጥ ሆነው ለ2000 ዓመታት የጠበቁልንን የቤተክርስቲያን አንድነት እኛ ሳንቸገር ለ3 ከፍለናታል። የባሰ አታምጣ አለች እምዬ ቤተክርስቲያን! የባሰ አታምጣ ማለት ታላቅ ጸሎት ነው። 

ወደ ፊት ቤተክርስቲያን ለስንት ይሆን የምትከፈለው? 


ቤተክርስቲያን የባሰ አታምጣ ያለችው ለዚሁ ነው። ከዚህም የባሰ አለና። ስለቀደሙት ክቡራን አባቶች በተናገርንበት አንደበታችን እንክርዳዶቹን ማየታችን ያሳዝነናል። አሁንም ክቡራን አባቶች ቢኖሩም በበዛው ስንናገር ግን ከስንዴው እንክርዳዱ ያመዝናል። ምርጥ እቃ የተባሉ ምርጥ ስንዴዎች እንዳሉ ግን መቼም አንዘነጋም!

በእምዬ አሜሪካ ያሉ ቤተክርስቲያንን እንደ ኳስ ያንቀረቀቡ ሰዎችን ስናስብ ያሳዝነናል። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ብዙ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾቻችን በውድ ዋጋ ለአሜሪካና ለአውሮፓ አብያተ ክለቦች ተሽጠዋል። አጥቂው የራሱን ጎል ለማግባት ቤተክርስቲያንን በሃይለኛው ይለጋታል። በእግሩ ለግቶ ያሰበው ጎል ባይገባ በጭንቅላቱ ደግሞ ይሞክራል። አቤት! ቤተክርስቲያንን የሚያንቀረቅቡ ኳስ ተጫዋቾች ብዛታቸው!! ችግሩ ደግሞ ኳሷ አንድ ብቻ መሆኗ ነው፤ ቤተክርስቲያን አንዲት ስለሆነች እነ ዮዲት የተጫወቱበት እነ ግራኝ አህመድና ሱስንዩስ የለጓት ኳስ እስከ ዛሬ አልተቀየረችም። ይህች ኳስ ወደ ፊትም የማትቀየር ኳስ ናት።

ወደ ዘመናችን ኳስ ጨዋታ እንመለስ። ሁሉም በየፊናው የራሱን ጎል ለማግባት ወደ ፊት ይሮጣል። ተከላካዩም ቢሆን የራሱን ጎል ለማግባት ወደ ፊት ይጋልባል። በረኛው ብቻ ቤተክርስቲያንን ይጠብቃታል። ጠባቂዋ ፈጣሪ ብቻ ቤተክርስቲያንን ይጠብቃታል። 

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/ 
Unlike ·  · Unfollow Post · Share · Edit
·                                  
·                                
·                                 38 shares
·                                  
o                                                       
Shewa Abu Ewnet sinegar (semi goro asteway lbona ysten.) K.H.Y.
o                                                       
Weldemesekel Endashaw Yegzabhire bete mekdes slhonche
o                                                       
Alemu Enyew kal hiwot yasemalen
o                                                       
Emu Adaragaews Antartar Anefra HAYEMNOT ANDET NAHE YAMGAMRYWAm YAMHARSHEWM YAORTWDKEX TAWAHEDW EMNT NAHE !!!YAEGZYIBEHAR LEgWHE HWYE BADDES KALTOHE ANSHE NAFE EGZYIBEHAR MASETWALN YADLAN AMEN AAAAAAAAAAAAAMMMMMMMEEEEEEEENNNNNNNNNNN
o                                                       
ዮኒዬ ቃለ ህይወትን ያሰማልን እንደአጋጣሚ ሆኖ ሰንበት ት/ት/ቤት ውስጥ የተሰጠንን ኢትዮፕያ እንግዶችን በመቀበሏ ተጠቅማላች ወይስ ተጎድታለች? የሚል Project እየሰራው ባለሁበት ሰአት ይህን ፅሁፍ በማንበቤ ደስ ብሎኛል። ተዋህዶ በተለያዩ ምእራፎች ያሳለፈችው ብዙና ብዙ ክስተቶች በታሪክ ማህደር ላይ ተመዝግበው አልፈዋልዛሬ ስለቆምንባት ቤተክርስትያን ብዙ የፍቅር ውለታ ተውሎልናል ምንም እንኩዋን ፈተና ቢበዛ በዘመናችን ይቅር ባይነትን ፍቅር ከኛ ይጠበቃል ቅዱስ ቄርልስ ስለንስጥሮስ መመለስ ይተጋ እንደነበረ ሁሉ እኛም ስለቤተክርስትያን ወንድሞች ህብረት እንፀልይ። አሜን+
July 13 at 6:56pm · Unlike · 6
o                                                       
Addis Hiwot Kala hiwotn yasemalenn!
July 13 at 7:35pm · Like · 1
o                                                       
o                                                       
o                                                       
Bitania Birhanu Leka sew selrote aykdmem: gulbetam seltagle aytlm: golyad wdkwal bdawit teter: ygna amlak semu kef ybel ykber. Ylum motwal silu norn: ylum tftwal silun beztn: alen begziabher ulun alfen: alen bgeta vlun alfn
July 14 at 7:02pm · Like · 1
o                                                       
Hiabraha Hi lemigebachew kezihm belay new. gin picturu bedemb aytaym
o                                                       
Desta Berhe ‎+ እግዚአብሔር የጻድቃን ቤት ይባርካል፡፡ምሳ- 3፡33
July 15 at 5:19pm · Like · 1
o                                                       
Hiwot Abraham bchernatu amlak ytabekat
o                                                       
Negede N Binyam Ewunet newu.
o                                                       
גרשון יגואר אוהב את זה
o                                                       
yes aythloatem.
July 16 at 5:34pm ·  · 1
o                                                       
Biruk Alemu min libelih esu yeegnan betekrstian bcha aydelem yemitebkew atfiwochuwanim chimir new yemitebkew yegziyabher sim lezelalemu yetebareke yhun!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
!!!!!!!!!
o                                                       
Bitania Birhanu ‎@yoni Yheh betcrstian debre amen teklhaymanot new aydl?
o                                                       
Shewa Abu Bemaynawets Mesret lay Temasrtalech ena....
o                                                       
o                                                       
Esayas H Yesus ewnet new
o                                                       
Messi Taye ewunet newu
o                                                       
o                                                       
Esayas H Yesus ewnet1000000*

==> “የዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎች”<==



ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ!



ከራሴ ጋር አጠር ያለች ስብሰባ አደረኩና አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰው በሞተ ቁጥር የሰፈሩ ሰው እትዬ ጣይቱን እድር ይግቡ እንጂ ብለው ሲመክሯቸው “እዲያ በሕይወት እያሉ ሳይረዳዱ ቀባሪን ለሚያበላ እድር ምን አስጨነቀኝ” ይሉ ነበር። የእድሩ ዳኛም “ጉድ መጣ ገንፎ ዛፍ ላይ ወጣ! የኛ
 ፈረንጅ!!” ብለው ሰዎች እንዲያግዟቸው በረጅሙ ሳቁ። እትዬ ጣይቱም ፈረንጅ እድር አለው እንዴ? ብለው ጠየቁ። የሚመልስ ሰው ግን አልተገኘም። “እናንተን ማስረዳት ቀባሪን ማርዳት እንዳይሆንብኝ እፈራለሁ” አሉ እትዬ ጣይቱ የእድር ዳኛውን በቆረጣ እያዩ። በአባባላቸው ሰው ሁሉ ሳቀ። “ማረኝ እንጂ አትመመኝ አይባልም” ይሉ ነበር እትዬ ጣይቱ። እውነታቸውን ነውኮ። “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ ነው መጨነቅ” አሉ እትዬ ጣይቱ! 

መቼስ የእትዬ ጣይቱ ጨዋታ አይጠገብም። በጨዋታቸውና በሙያቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። እንዲያውም የእትዬ ጣይቱን ምግብ በልቶ ማን እጁን ይታጠባል ይባልላቸዋል። ዛሬም ምርጥ ምርጡ በየዓይነቱ ጠረጴዛው ላይ ተደርድሯል። እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን ጠሩና እኔ በልቻለው አቅርቡና አብራችሁ ብሉ አሏት። ኤፍራታም ኧረ አልራበንም በኋላ እንበላለን አለች። ጉድ እኮ ነው የሱን ሆድ መች አየሽው? አሉ እትዬ ጣይቱ። አባባላቸው አሳቀኝ። “ከአንድ ብርቱ ሁለት ገልቱ” እስኪ አንድ ላይ ብሉ ብለው በየዓይነቱን አቀረቡልን። እትዬ ጣይቱ ምሳሌያዊ ንግግራቸውን አገለባብጠውት እያዝናኑ ስለሚያስተምሩ እወዳቸዋለሁ። “ነገር በብርሌ ጠጅ በምሳሌ” አሉ እትዬ ጣይቱ! ዛሬ እትዬ ጣይቱ የነገሩኝ ታሪክ ይህ ነው፦

በአንድ ወቅት የእትዬ ጣይቱ ባለቤት አቶ ይድነቃቸው ገበሬዎች ከሚዘሩት ከአፈር ጋር የተቀላቀሉትን ጤፍ ሰበሰቡና ወቀጡት። ይህን ጊዜ ንጹህ ጤፍ ከአፈሩ ተለየ። አቶ ይድነቃቸው ይህን ጤፍ በሁለት ብር ሸጡና ዶሮ ገዙ። ዶሮውን አስታቅፈው ብዙ ጫጩቶችን አገኙ። ሲቀጥልም ዶሮውን በአምስት ብር ሸጡና በግ ገዙ። አቶ ይድነቃቸው ሰው ሁሉ እስኪደንቀው ድረስ በጉን አደለቡት አሰቡት። የሰባውን በግ ሸጡና አነስተኛ የእርሻ መሬት ገዙ። ሰው ሁሉ በአቶ ይድነቃቸው ተደነቀ። ከዛማ የእርሻ ምርቱ እንደ ጉድ ተስፋፋ። አቶ ይድነቃቸው የብዙ በጎች የብዙ ዶሮዎች የብዙ እንስሳት ባለቤት ባለሀብት ሆኑ! ሰው ሁሉ ስለተደነቀባቸው “አቶ ይድነቃቸው” የሚል ስም ወጣላቸው። ከጤፍ ፍርፋሪ የተከበሩ ባለሀብትም ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው ድል ያለ ሠርግ ደግሠው እትዬ ጣይቱን አገቡ። አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታንም ወለዱ።


በአቶ ይድነቃቸው የእርሻ ካምፓኒ ብዙ ገበሬዎች ተቀጠሩ። ከገበሬዎቹ መካከል አንዱ በጎቹን እየተንከባከበ ያደልባቸው ነበር። በጎቹ ቢታዩ ለዓይን የሚማርኩ ቢበሉ ለምላስ የሚጣፍጡ ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው እጅግ ተደነቁና ይህን ገበሬ አስጠሩት። ገበሬውም ለጥ ብሎ እጅ ነሳና “መጥቻለሁ ጌታዬ” አለ። አቶ ይድነቃቸውም ታታሪው ገበሬ ሆይ ስራህ ድንቅ ነው! በጎቹን በሚገባ ተንከባክበሃልና! በጣም የሚገርመኝ ግን በጎቹን ትቀልባቸዋለህ ታደልባቸዋለህ እንጂ ምን አወቁ? ሃይማኖታቸው ምንድን ነው? አትልም። ዛሬም ወላጆች ለልጆቻቸው ወተት ብቻ ምግብ ብቻ መግበው ስለ ሃይማኖታቸው ስለ አስተሳሰባቸው ካልተጨነቁ በግ አደለብን እንጂ ልጅ አሳደግን ማለት ከቶ አይችሉም! ልጆች ምን አወቁ? ምን ያስባሉ? ብለው ካልጠየቁ እውነትም በግ እያደለቡ ነው! አሉ እትዬ ጣይቱ ገና በጠዋቱ። እኔና ኤፍራታም በአባባላቸው ሳቅን።

እትዬ ጣይቱ አያችሁት ያን ልጅ? አሉ ድንገት ወደ ጓሯቸው እየተመለከቱ። በግ ለልጅዋ ወተት ስትመግብ አንድ ትንሽ ልጅ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጎንበስ ብሎ አተኩሮ ይመለከት ነበር። ለሚያየው ሰው “እኔም ወተቱን ባገኘሁት” የሚል ይመስል ነበር። ኤፍራታ ቶሎ ብላ በያዘችው ሞባይል ፎቶ አነሳችው። ኤፍራታ በሳይንስ የተማረችውን አስታወሰችና “እናት ለልጅዋ በመጀመሪያ የምታጠባው ወተት ማለትም እንገር /colostrums/ የሚባለው ለሕጻኑ ጤንነትና እድገት እጅግ ወሳኝ ነው” አለችን። ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ሳይሆን “የዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎች” እንዳይሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል አሉ እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን በስስት እያዩ።