Sunday, 30 March 2014

ከቀልድ ዓለም!

እንኳንስ ዝናቡ መብረቁም አልፏል አለች ፀሐይ!

የማያልፍ የለምና!

ክብርት ሚስትህን አክብራት

ተንከባከባት

አድምጣት

ቆንጆ  ነሽ በላት

ባትላት ግን ችግር የለውም!

ጎረቤትህ ይላታልና!”

ሰምተሃል!

Sunday, 2 March 2014

ከቀልድ ዓለም!

 “አይ ጥልያን፤ ደግሞ ብለሽ ብለሽ አይንሽን ጨፍነሽ መጣሽ

አዲስ አበባ የአቢዮት በዓሏን እያከበረች ያለች እስኪመስል ድረስ በቀይ ቀለም አሸብርቃለች፡፡ ምንድን ነው ይሄ ነገር ? ብየ ስጠይቅ፣ ዛሬ የቫለንታይንስ ቀን ነው አሉኝ፤ ….. አሃ፣ ታድያ አቢዮትንና ፍቅርን ምን አገናኛቸው ? …. ፍቅርንና ቀይ ቀለምን ምን አጎዳኛቸው ?... መጠየቄ አልቀረም፣.. እንዲህ ነው አሉ፤…. ቀይ የደም ቀለም አይነት ነው፤ ደም ደግሞ መስዋእትነትን፣ ስቃይን፣ ታማኝነትን(kind of blood oaths..) ቤተሰባዊ ትስስርን ይወክላል አሉኝ፤ እሽ፤…. ጾታዊ ፍቅር ቀይ ነው፣ ምክንያቱም ከሚወዱት ጋር አብሮ ለመሆን ያለን ከፍተኛ ፍላጎት፣ እጅግ በጣም ጽኑ የሆነ ስሜትን ይገልጻል፤ በተጨማሪም በሰርግ ማግስት ድንግልናን ማጣት (የአንሶላው ላይ ብለድ ሼድ ነገር መሆኑ ነው እንግዲህ፣ …. ወይንም ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ የሚባለው ነገር.. ትዝ አላችሁ አይደል ? ….. አሁን አሁን እንኳን ቀርቷል መሰለኝ)…. ይገልጻል አሉኝ፤.. እስከ አሁን ድረስ አልገባኝም…. የፍቅርና የብር አምባር ነገርም ግንኙነታቸው አልተገልጦልኝም…… 

አሄሄ…. 

የሀገሬ ባላገር በየገጠሩ የተበተኑትን የቻይና መንገድ ሰራተኞችን ሲያይና የመልካቸውን ቅላትና የአይናቸው ማነስ አስገርሞትአይ ጥልያን፤ ደግሞ ብለሽ ብለሽ አይንሽን ጨፍነሽ መጣሽአለ አሉ…. ድጋሚ በጣልያን የተወረረ መስሎት አኮ ነው፡፡ ክብር ለጀግኖች አባቶቼ ይሁንና! ጣልያንስ ድጋሚ በክፉ እንዳያየኝ አድርገው መልስ ሰጥተውልኛል ……. አይ ከንቱ ድካም ነው፤ ለካንስ ጣልያን ቂሟን አልዘነጋችም ኖሮ ይሔው ዛሬ ቅዱስ ቫለቲነስ የተባለ ቄሷን ይሁን ሰይጣኗን ልካ የሀገሬን ሰው በእንብርክክ አስኬደችው፡፡ 

የሆነው ሆኖ በአገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ተፋቀሩ ተዋደዱ! የምር ፍቅር በፍቅር ሁኑ!

ጨው አይደለ በምላሴ ልቀምሰው
  ትኛው ነው የሚታመነው ሰው?

ፕሮቴስታንት ሴቶች ሆይ ፀጉር ሳይሸፍኑ ጸሎት ይገባልን?
አንዲት ፕሮቴስታንት እህቴን ለምን ፀጉርሽን ሳትሸፍኝ ትጸልያለሽ? ስላት አንዱ  ፓስተር መጣና  ራሱን ተከናንቦ   የሚጸልይ  ወንድ የተረገመ  ነው ተብሏልና  ካህናት  ለምን ራሳቸውን  ይከናነባሉ???  አለ። ልጅቱም የነብርን ጅራት  ከያዙ  አይለቁ  አለችና  ለህሊናዋ  መልስ  ያገኘች ስለመሰላት ደስ ብሏት እየፎከረችብኝ  ሄደች።

 ዘመዶቼ ሆይ ለሥጋችሁ ምኞት ስለምን ምክንያት ፈለጋችሁ? አንድ እህቴ ለሕሊናዋ ምክንያት አግኝታ ፀጉሯን ሳትሸፍን እንደ ፍላጎትዋ ትሆን ዘንድ በጣም ደስ እንዳላት ስላየሁ ዝም አልኩ። ይህ የብዙ ዘመን የህሊናዋ ጥያቄ ነበር ማለት ነው። ታድያ ለምን ከህሊናዋ ስትጣላ ኖረች?

 ካህናቱ ጥምጣም ያደርጋሉ፤ ካህኑ ኢያሱ በራሱ ላይ ይጠመጥም ነበርና። እነሆ መልአኩ ንጹህ ጥምጣም ጠመጠመለት ይላልና ካህናቱ የሚጠመጥሙት ለዚህ ነው። እህቶች ሆይ ኢስላም እህቶች ሲከናነቡ ጌታን ተከታይ መንፈሳዊያኑ ምክንያት ከምትፈልጉ ሥጋዊ ምኞታችሁን መቆጣጠር እንዴት አቃታችሁ? ዘፀ28:40 ቆቦችንም ለክብር ታደርግላቸዋለሀ...41 በክሀነት እንዲያገለግሉ ዘሌ8:9 እግዚአብሄርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያዉን አደረገ...የተቀደሰዉንም አክሊል ዘካ6:11 አክሊሎችንም ስራ በታላቁም ካሀን ...ራስ ላይ ደፋ 1ነገ21... አልተሳሳትንም!!!

ትርፍ ነፍስ
- - - - - - - - - - - - -
ሳቅልኝ!'' ብትይኝ
ልክ እንደ ማሽላ ውስጤ እያረረ
ለይምሰል ለይምሰል ስቄልሽ ነበረ!
''
አልቅስ''ብትይኝም
ምጥ አማጥጬ
ሆምጣጤ ጨልጬ
አልቅሼ ነበረ!
''
ጩህ!'' ብትይኝ ውዴ
ጉሮሮዬ ዝሎ
አንደበቴ ሰሎ
ጩሄልሽ ነበረ!
ግና - - - - -
''
ሙትልኝ!'' እንዳልሽኝ ዛሬ ሰምቻለሁ
ትርፍ ነፍስ ስትኖረኝ እሞትልሻለሁ!!

***** ሰይጣኔ *****

የሰው ልጅ ሲናደድ ቁጣ ቁጣ ሲለው፣
’’
ሰይጣኔን አታምጣው!’’
ብሎ የሚያስጠነቅቀው፣
በቅርብ ርቀት ላይ ከጓሮ ያስቀመጠው፣

ሲጠራ ሊመጣ በተጠንቀቅ ቆሞ የሚጠባበቀው፣
ለካስ እያንዳንዱ፣ የግሉ የሆነ፣ አንድ አንድ ሰይጣን አለው፡፡

The Victory of Adwa 118th Anniversary

እጅክ ላይ ያሰረካት ባንዲራ የማን  ናት?

ትላንትና  ማታ በአውሮፕላን ሆድኩና
ነጮቹ ከበውኝ ጥያቄ  አበዙና
እጅክ ላይ ያሰረካት  ባንዲራ የማን  ናት?
አሉና  ጠየቁኝ፤ ነጮች መጠየቅ ልምዳቸው ነውና።

ይህቺ ባንዲራማ ………ብዬ የእጄን ባንዲራ  አይቼ   ቀና  ሳልል ገና
ሐሳቤን ሳልፈጥም በሐሳብ ፕሌን ጭልጥ ብዬ  ሄድኩና
ድንገት ስነቃ  ፕ ሌ ኑ ተጠልፎ ሰዉ ተተራምሶ  ግራ  ተጋባና
ሐሳቤን የሚሰማ አንድ ጀግና   አንድ ሰው ጠፋና
እኔው ለራሴው አወራሁ  ከራስ ጋ  መሰብሰብ አይከፋምና።

እጅክ ላይ ያረካት ባንዲራ የማን  ናት?

ይህቺ ባንዲራ  ናት እድለኛ
የተከበረችቱ በክቡራን አርበኛ
አልኩና  ጀመርኩ ሰለ  ሀገሬ ስለ እምዬ
ታሪኬን ዘክዝኬ  ለመንገር ቸኩዬ

ይህቺ ባንዲራማ…………..

አጥንት ተከስክሶ  ደም የፈሰሰባት
በጀግኖች አበው የተፎከረባት የተሸለለባት

ይህቺ ባንዲራማ............

ያንን ነጭ ሊጥ ያንን  ጥልያንን ያንበረከከች
አሸብርካ በጉልበት በእንብርክክ ያስኬደች
ለጥቁር ህዝብ ለአፍሪካ መኩራሪያ  የሆነች

ይህቺ ባንዲራማ............

የነፃነቴ ልብስ አቅፌ  የምለብሳት
የምትመች የምትሞቀኝ ከልብ የምወዳት
ዘወትር ቀን ማታ  ከሃሳቤ  የማልረሳት
ክብርት ባንዲራዬ  ይህችኛይቱ ናት።

ከዚህ በኋላማ ምኑን ልንገራችሁ?

ነሸጥ አረገኝ  የአባቶቼ ስሜት
ፎክር ፎክር አለኝ ሳላስበው ድንገት
ይኸው ፎከርኩ በነጮቹ መሃል
የነፃነት ማማ ከጥቁሮች መካከል
ይህች ናት ሀገሬ  ባርያ  ነኝ  የማልል
ኩሩ ኢትዮጲያዊ መሆን ቀላል ደስ ይላል!

አቧራው ጨሰ  ፉከራው ቀጠለ ተቀወጠ እንደ  ጉድ
  
ገለል በሉና ገለል አርጓቸው
ወደመጡበት ወዳገራቸው
ለነዚህ ጣልያኖች መድኃኒት ስጧቸው
የሚያስቀምጥ ሳይሆን የሚያስመልሳቸው
አርኩም ይሄድና ሶልዲውም ያልቅና
ያስተዛዝበናል ይኼ ቀን ያልፍና!
ምንሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፡
ግብሩ አሽከር ነበር ያን ጊዜ በሻ።
አልኩና  ፎከርኩ ኡፈይ የልቤ  ደረሰ!

ይህቺ ባንዲራማ

ደም የፈሰሰላት በደም ስሬ  ያለች
በእጄና  በአንገቴ  በክብር  የታሰረች
በደረቴ  ገብታ በ ል ቤ  የታተመች
ክብርት ባንዲራዬ  በአጭሩ  ይህች ነች።

‹‹
ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ››

Home is where the heart is….East, west, home's best !
Memar Zele'alem
Fb 2 blog…..Blog 2 fb

Ethiopia uncolonized powerful country........We Ethiopians pride ourselves as the only independent people in Africa.

The Battle of Adwa saw Ethiopian forces defeat the Italians in the decisive engagement of the First Italo-Ethio War.

Battle of Adwa Overview

Italians

General Oreste Baratieri

17, 700 men
56 guns